በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት (መሀል አምባ) የወረዳውን ማዘጋጃ ቤት የቢሮ ህንፃ ግንባታ ለማሰራት GC/BC ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ ተቋራጮችን የጋበዘበት ሀገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ (ቁጥር GGWW/007/2019)።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት መሐል አምባ
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ሀገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
መለያ ቁጥር GGWW/007/2019
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን በገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ለገ/ጉ/ወ/ወረዳ/ከ/ል/ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት ለጎራ ማዘጋጃ ቤት የቢሮ ግንባታ ለማስራት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። ስለሆነም ተጫራቾች --
- የዘመኑ ንግድ ፈቃድ ያሳደሱ የቫት እና ቲን ነምበር ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙት ጨረታ ሰነዱን ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆኑ ከድርጅቱ ህጋዊ ውክልና ይዘው መምጣት አለባቸው።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 25ኛው ተከታታይ ቀናት እስከ 8:00 ሰአት ድረስ የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ ብር ብቻ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መሀል አምባ ከተማ ገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
- የመወዳደሪያ ደረጃቸውም GC/BC ደረጃ 5 እና ከዛ በላይ የሆነ ተቋራጮች
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ብር 300000 ( ሶስት መቶ ሺህ ብር) ብቻ በገ/ጉ/ወ/ፋይናንስ ፅ/ቤት ስም ማሰራት አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት ሀ/ ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ቴክኒካል በሚል በመለየት ለ/ ለፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ፋይናንሻል በሚል በመለየት በሰም በማሸግ ከላይ የተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንቱ ጋር በማድረግ በሰም በማሸግ ቴክኒካል ዶክመንት በሚል በመለየት ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 25(ሀያ አምስት ) ተከታታይ ቀናት መሀል አምባ የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመምጣት ለጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው ሰነድ በ25ኛው ተከታታይ ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ይታሸጋል ፡ ከቀኑ 8:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- አሰሪው መስሪያቤት ለጨረታው አሸናፊ ድርጅት ቅድመ ክፍያ የማይከፈል መሆኑን እና ስራው ደግሞ በደረሰበት ታይቶ ና ተረጋግጦ የደረሰበት ክፍያ የሚፈጸም መሆኑን።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡-
- በአፈፃፀም ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ድርጅቶች መወዳደር አይችሉም ፡
- በወረዳው ውስጥ ፕሮጀክት ይዞ ስራውን ያልጨረሰ ተጫራች መወዳደር አይችልም ።
- ተጫራቾች ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ከአሰሪው መስሪያ ቤት የሳይት ምልከታ ማየታቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው ።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በአል ወይም ቅዳሜ ና እሁድ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል።
ለበለጠ መረጃ፡- የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ስልክ ቁጥር 0113360162/146 ይደውሉ።
ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን በገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት መሀል አምባ
Summary
Gedebano Gutazer Wolene Woreda Finance Office (Gurage zone, Central Ethiopia) invites GC/BC grade 5 and above contractors to build a municipal office building. No advance payment; bidders must present a site visit letter.
