ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት (ቢሾፍቱ) የቢሮ እድሳት (Office Renovation) ስራ በማቴሪያል አቅርቦት ለማሰራት GC-6/BC-5 እና ከዚያ በላይ ተቋራጮችን የጋበዘበት ሀገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ (ቁጥር NVI 02/2019)።
NATIONAL VETERINARY INSTITUTE (ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት)
ለቢሮ እድሳት (office Renovation) የወጣ ሀገር አቀፍ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር NVI 02/2019
ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት የቢሮ እድሳት ሥራ አስፈላጊ ማቴሪያል አቅርቦት፣ የጥገና፣ የማሻሻያና የማጠናቀቂያ ሥራዎችን በመመሪያ ቁጥር 1070/2017 እና በተቋሙ የግዥ አሠራር ሥርዓት መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተገለፀውን መስፈርት የሚያሟሉ ህጋዊ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት የቫት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN ሠርተፍኬት፣የግብር ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሥራ ተቋራጭነት ሥራ ደረጃ GC-6/BC-5 እና ከዚያ በላይ ሆኖ ከገቢዎች ሚኒስቴር ወይም ገቢዎች ቢሮ የተሰጠ በጨረታ መሳተፍ እንደሚችል የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታውን ሰነድ ማስታወቂያው መጀመሪያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከኢንስቲትዩቱ ገዝተው መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የቴክኒክ ሰነድና የሚጫረቱበትን ዋጋ ለየብቻው በመሙላት የድርጅታቸውን ማሕተምና ፊርማ አድርገው እንዲሁም ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የዋጋቸውን 2% በሲፒኦ ብቻ በማስያዝ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ታህሳስ 02 ቀን 2019 ዓ.ም በኢንስቲትዩቱ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል ቢሮ ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከጠዋቱ 2:00 ሰአት እስከ 11:00 በሥራ ሰዓት ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ታህሳስ 02 ቀን 2010 ዓ.ም በመ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ከጠዋቱ 4:00 ተዘግቶ 4:30 ይከፈታል።
- ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋም ሆነ በሌላ የጨረታ ጉዳይ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
- ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ውስጥ የተገለፁትን መስፈርቶች በሙሉ ማሟላት አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚሰራውን ሪኖቬሽን ሥራ ቦታው ድረስ በአካል በመገኘት መመልከት ይችላሉ።
- አሸናፊው ተጫራች ውል በመፈረም ስራውን በአጭር ጊዜ ውስጥ መጀመር ይኖርበታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ቢሾፍቱ ከተማ ከመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ አለፍ ብሎ ከእንስሳት ሕክምና ፋኩልቲ አጠገብ።
ለበለጠ መረጃ ለማግኘት 09-76-07-88 88/ 09-88 38 83 15 መጠየቅ ይቻላል።
ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት
Summary
National Veterinary Institute (Bishoftu) invites GC-6/BC-5 and above contractors to carry out office renovation, including material supply, repair, upgrading and finishing works. Bidders need a renewed licence, VAT, TIN and tax clearance.
