Tender Detail

Tender Details

  • Company የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን
  • Address ወልቂጤ ከተማ ወደ ወልቂጤ ኢንዲስትሪያል ኮሌጅ በሚወስደው አስፋልት መንገድ ላይ የድሮው የወልቂጤ ከተማ ስፖርተኞች ማደርያ ጊቢ ውስጥ : በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት : ኢትዮጵያ, Phone: 011 365 9932
  • Website
  • Deadline07 Dec 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Price300(ሦስት መቶ ብር)
  • Bid Securityብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በባንክ ዋስትና ወይም CPO
  • opening dateበዚያኑ ቀን ከቀኑ 8:30
  • Sector Energy , Fuel and Lubricants

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን በስሩ ላሉት ዲስትሪክቶች ለከባድ ማሽነሪና ቀላል ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚሆን ልዩ ልዩ ዘይትና ቅባት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ያወጣው ማስታወቂያ (ቁጥር ዘይ/ቅ-1-/2019)።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን

Add to calendar Google Calendar Download .ics

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ዘይ/ቅ-1- /2019

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን በሥሩ ላሉት ዲስትሪክቶች አገልግሎት የሚውሉ ለከባድ ማሽነሪና ቀላል ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚሆን ልዩ ልዩ ዘይትና ቅባት ግዥ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችለውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የንግድ ሥራ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት፣ መንግስት መ/ቤቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚያስችል የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች በታሸገ ኢንቨሎፕ የፋይናንሻል ዋና እና ሁለት ኮፒ የቴክኒካል ፕሮፖዛሉን ዋና እና ሁለት ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ ኦሪጅናል እና ኮፒ 1፣ ኮፒ 2 በማለት እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በተለየ ፖስታ ለብቻው በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00/ሦስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከባለስልጣኑ ዋና መ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
  4. የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሰረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው።
  5. አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት ቀን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ድረስ ይሆናል። ጨረታው በዚያኑ ቀን ከቀኑ 8:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
  6. ተጫራቾች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዘንድ ዕውቅና ካላቸው የፋይናንስ ተቋም በቅደመ ሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ሲ ፒ ኦ /c.p.o/ ብር 500,000.00/ አምስት መቶ ሺህ ብር ብቻ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሰረት ጨረታውን ማቅረብ አለባቸው። ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም። እንዲሁም ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ይሰረዛሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ይወረሳል ለወደፊቱም መ/ቤቱ በሚያወጣው የግዥ ጨረታ እንዳይሳተፉ ይደረጋል።
  8. ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለ45 ቀናት ፀንቶ መቆየት አለበት።
  9. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. ለበለጠ መረጃ የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን ግዥና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም የስልክ ቁጥር 0113659932 ወልቂጤ- ኢትዮጵያ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን

Summary
Central Ethiopia Region Roads Authority buys various oils and lubricants for the heavy machinery and light vehicles of its districts by open tender, open to any supplier regardless of nationality with a relevant licence, supplier registration and VAT.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender