የካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ (ቦንጋ) የሞተር ሳይክል ጎማና ካላማንዳሪ፣ የቪ 8 መኪና መለዋወጫ ዕቃዎች እና የተሽከርካሪ ዘይትና ቅባት ግዥ በ3 ሎት ያወጣው የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ (ቁጥር ግ/ጨ/05/2019)።
ካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ (ቦንጋ)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታቁጥር-ግ/ጨ/05/2019
የካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በሎት በመከፋፈል 2019 በጀት ዓመት በዞን ማዕከል ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት -1- የተለያዩ ሞዴል ላላቸው የሞተር ሳይክል ጎማና ካላማንዳሪ ለመግዛት! ሎት -2- የቪ 8 መኪና መለዋወጫ ዕቃዎች ግዥ እና ሎት -3- የተለያዩ ሞዴል ላላቸው ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚውል ዘይትና ቅባት እስከ በጀት ማብቂያ ድረስ ማለትም ሰኔ 30/2019 ዓ/ም ዋጋ ፀንቶ የሚቆይ ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሠረት፡-
- ሎት .1. የተለያዩ ሞዴል ላላቸው የሞተር ሳይክል ጎማ ካላማንዳሪ ለመግዛት!
- ሎት .2. የቪ. 8 መኪና መለዋወጫ ዕቃዎች ለመግዛት እና
- ሎት .3. የተለያዩ ሞዴል ላላቸው ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚውል ዘይትና ቅባት ለመግዛት ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ ለማወዳደር ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ፡-
- የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ &በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ&የአቅራቢነት ሰርቲፊኬት&የቲን/TIN/! ከገቢዎች ግብር ስለመክፈላቸው የተሰጠ ማስረጃ እና የቫት ተመዝጋቢነት ሰርቲፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች የጨረታ ዶክመንት ሊገዙ ሲመጡ ኦርጅናሉን እና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ አቅርበው እንዲመሳከር የማድረግ ግዴታ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለሁሉም ሎቶች ለእያንዳንዳቸው የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500/አምስት መቶ ብር/ ካፋ ዞን ገቢዎች ባለስልጣን መምሪያ ቀርበ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ለተከታታይ አስራ አምስት /15/ ለተከታታይ ቀናት ካፋ ዞን ፋይናንስ መመሪያ ግዥ ንብ/አስ/ሥራ ሂደት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለእያንዳንዳቸው ሎት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO(Certified payment order) &ጥሬ ገንዘብ ወይም ቼክ ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ ከፋይናንሻል ፖስታ ውስጥ በማስገባት በካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግ/ ንብ/አስ/ ስም በማሰራት ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ለሎት.1 ፣ ለሎት.2 እና ለሎት-3- ተጫራቾች ፋይናንሻል የጨረታ ዶክመንት ተገቢዉን ፊርማ እና ማህተም በማሳረፍ ለየብቻ እንዳንድ በሰም/በሙጫ/ በታሸጉ ፖስታዎች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት በካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥ ንብ/አስ/ በመቅረብ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- የጨረታው ሳጥን ሁሉም ሎቶች በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3:30 ሰዓት ታሽጎ በዚያዉ ዕለት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ከጠዋቱ በ4:00 ሰዓት ይከፈታል።የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል። በመክፈቻው ዕለት የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮች ያለመገኘት የጨረታ መክፈት ሂደት አያስተጓጉልም።15ተከታታይ ቀናት የተባለው ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም በዓላት ቀን ጨምሮ የሚቆጠር ነው።
- ተጫራቾች ሁሉንም ሎቶች ያሸነፉበትን የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ /performance bond/ ለማስያዝ ፈቃደኛ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች አሰሪዉ መ/ቤት ያዘጋጀዉን የተጫራቹን መመሪያ እና የቴክኒካል ዶክመንት መጠይቅ ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
ካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ቦንጋ
Summary
Kaffa Zone Finance Department (Bonga, South West Ethiopia) buys for zone sector offices in 3 lots: motorcycle tyres and inner tubes, V8 vehicle spare parts, and vehicle oils and lubricants, with prices valid to the end of the budget year.
