የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት በቡርጂ ዞን ሶያማ ከተማ የሚገኙ የዳቦ ማምረቻ ማሽነሪዎችንና ጀነሬተርን በመነሻ ዋጋ ብር 7,237,089.33 ለመሸጥ/ለማከራየት ያወጣው የሁለተኛ ዙር ዝግ ጨረታ ማስታወቂያ።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት
የሁለተኛ(2ኛ) ዙር ዝግ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በሊዝ ፋይናንሲንግ ለአቶ መሐመድ ቡራ የሰጠው የዳቦ ማምረቻ ማሽኔሪ እና ጀነሬተር ተከራዩ የኪራይ ክፍያውን በካፒታል እቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ ውሉ መሰረት ሊከፍል ባለመቻሉ በአዋጅ ቁጥር 103/1990 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ተረክቦ ባሉበት ሁኔታ በሐራጅ/ መሸጥ/ማከራየት ይፈልጋል።
| ተ.ቁ | የንብረት አይነት | ብዛት |
|---|---|---|
| 1 | Rotary oven 14 Try | (01) set |
| 2 | Volumetric Dough Divider የሊጥ ማከፋፈያ | (01) set |
| 3 | Mixer የሊጥ መቀላቀያ | (01) set |
| 4 | Molding Machine የሊጥ ቅርጽ ማውጫ | (01) set |
| 5 | Brade slicer የዳቦ መቁረጫ | (01) set |
| 6 | French tray with trolley | (02) set |
| 7 | Flat tray with trolley | (02) set |
| 8 | Diesel Generator | (01) set |
ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ፡ በደ/ኢ/ክ/መ ቡርጂ ዞን፤ ሶያማ ከተማ አስተዳደር፤ 02 ቀበሌ ክልል ውስጥ በተቋቋመው በአቶ መሐመድ ቡራ(በተከራዩ) የዳቦ ማምረቻ ቦታ
ዝግ ጨረታ መነሻ ዋጋ በብር፡ 7,237,089.33
ቦታ፡ በደ/ኢ/ክ/መጋሞ ዞን፤አርባምንጭ ከተማ በሚገኘው ዲስትሪክቱ ቢሮ
ቀንና ሰዓት፡ ህዳር 30 ቀን 2019 ዓ.ም 4:00-6:00
የጨረታ ሁኔታ፡ ሁለተኛ (2ኛ) ዙር ዝግ ጨረታ
ማሳሰቢያ
- በዝግ ጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ስምና አድራሻ በመጥቀስ፣ የዲጂታል መታወቂያ ኮፒ፣የጨረታውን መነሻ 1/4ኛ ወይም 25% በኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት ስም የተዘጋጀ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) አያይዞ ማቅረብ ይጠበቅበታል።ከዚህ በተጨማሪ ገዥው የሚገዛበትን ዋጋ በመግለፅ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ ህዳር 29 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 10:30 ሰዓት ድረስ ማመልከቻ ማስገባት ይችላል።
- ንብረቱ የሚገኘው በደ/ኢ/ክ/መንግስት ቡርጂ ዞን፤ ሶያማ ከተማ አስተዳደር፤ 02 ቀበሌ ክልል ውስጥ በተቋቋመው በአቶ መሐመድ ቡራ (በተከራዩ) የዳቦ ማምረቻ ቦታ ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው።የዝግ ጨረታ አሸናፊ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን (VAT)፣ ንብረቶቹን በጥሬ ገንዘብ ወይም እጅ በእጅ ሽያጭ የሚገዛ ከሆነ ከቀረጥ ነፃ መብት የመጠቀም ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል።ከቀረጥ ነፃ የመጠቀም መብት ከሌለው በመንግስት በህግ የተወሰነውን ታክስ ጨምሮ የሚጠየቅ ማንኛውንም ክፍያ በቅድሚያ በመክፈል ንብረቱን ይረከባል።
- ንብረቱን ሙሉ በሙሉ በሽ/በጥሬ ገንዘብ ለመግዛት ተወዳድሮ ያሸነፈ ተጫራች ንብረቱን ይረከባል፤፤በዝግ ጨረታ መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም አካል (ግለሰብ፣ ተቋማት፣ ወይም አነስተኛና መካከለኛ ማህበራት) ከቀረጥ ነፃ የመጠቀም ተመሳሳይ ዕድል ያለው ከሆነ የመጠቀም መብቱ በንብረቶቹ ላይ የሚያስከፍለውን የጉምሩክ ቀረጥ ለመክፈል ፍቃደኛ የሆኑ ሁሉ በዝግ ጨረታ መሳተፍ ይችላል።
- ንብረቱን በከፊል ለመከራየት የሚፈልግ ተጫራች ከሆነ ቢያንስ ያሸነፈበትን ዋጋ 20% ቅድሚያ በመክፈልና የባንኩን የሊዝ ኪራይ መስፈርት በማሟላት በ15 (አስራ አምስት )ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ የማሽኖቹን ኪራይ ውል መፈረም ይኖርበታል።ሆኖም ግን በተሠጠው ጊዜ ውስጥ ግዴታውን ካልተወጣ የዝግ ጨረታ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለባንክ ገቢ ይደረጋል።ለተሸነፉ ተጫራቾች በጨረታው ያስያዙት የክፍያ ማዘዣ ሰነድ ሲፒኦ (CPO) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
- ንብረቱ በባንኩ የካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ መስፈርት መሰረት የመከራየት ዕቅድ ያለው ተጫራች የባንኩን ካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ ፕሮግራም ተጠቃሚ መሆን ይጠበቅበታል።የዝግ ጨረታ አሸናፊ ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ንብረቱን ለማስተዳደር የሚወጡ የጥበቃና ሌሎች ወጪዎችን የማሸፈን ግዴታ ይጠበቅበታል።
- የዝግ ጨረታ አሸናፊ የካፒታል ዕቃውን ካለበት ቦታ ወደ ሚፈልግበት ቦታ ማጓጓዝ ወጪ፣የጉዞ ኢንሹራንስ፣ስራ ማስጀመሪያና ተያያዥ ወጪዎችን ገዥው ይከፍላል።የዝግ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪል በተገኙበት ህዳር 30 ቀን 2019 ዓ.ም ጧት 4:00 እስከ 6:00 ሰዓት በኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ይደረጋል።
- ስለንብረቱ ሁኔታ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 046-181-0606 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል።ንብረቶቹን መጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች በዝግ ጨረታ ቀን በፊት ባሉት ጊዜያት በባንኩ ቀጠሮ በመያዝ ንብረቶቹ በሚገኙበት የዳቦ ማምረቻ ቅጥር ግቢ በአካል በመቅረብ መጎብኘት ይችላሉ።ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ የዝግ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት
Summary
Development Bank of Ethiopia, Arba Minch District, holds a second sealed-bid sale or lease of repossessed bakery machinery (rotary oven, dough divider, mixer, moulder, slicer, trays) and a diesel generator located in Soyama town, Burji zone.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
