Tender Detail

Tender Details

  • Company በጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address ጅግጅጋ ከተማ ፡ ሶማሌ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0913220473
  • Website
  • Deadline24 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Price100(አንድ መቶ ብር) በአክሽን ኢትዮጵያ
  • Bid Securityለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) CPO
  • opening date15/03/2019 ከረፋዱ 4:00 ሰዓት (በኦንላይን)
  • Sector Rent , Vehicle Rent , Sales , Disposal Sale

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ያወጣው ማስታወቂያ።

በጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን ተሽከርካሪዎቹን ከ11/03/2019 ዓ.ም ጀምሮ ሳምፕል በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይገልፃል።

ማሳሰቢያ:- ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤

ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች:-

  1. ለተሽከርካሪ የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፤ ማንኛውም ተጫራች 100 ብር በመክፈል ከአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ።
  2. በሐራጅ ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) በተለያዩ ባንክ በጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት ስም ሲ.ፒ.ኦ. በማሰራት ያሰሩበትንም ሲ.ፒ.ኦ. በአካል ወደ አክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን አክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።
  3. ለሐራጅ ጨረታ ቅ/ጽ/ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ያለው ከሆነ ከመነሻ ዋጋ ተነስቶ እንዲሁም መነሻ ዋጋ የሌለው ከሆነ ተጫራቹ የራሱን መነሻ በማስቀመጥ በኦንላይን በአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
  4. ተጫራቹ በጨረታው አሸንፎ የገዛውን ተሽከርካሪ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ የሚረከብ መሆን አለበት።
  5. ተሽከርካሪውን አሸንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
  6. በጨረታው ያላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
  7. አሳማኝ የሆነ ምክንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይችላል።
  8. ማንኛውም ተጫራች ተሽከርካሪውን ካሸነፈ በኋላ ከጅግጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈልግ እንደየቦታው ርቀት በቀን ገደብ መሸኛ ሊሰጣቸው ይችላል።
  9. ተጫራቹ ተሽከርካሪውን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም።
  10. የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 05 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ15/03/2019 ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።
  11. የአክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር 09-05-11-55-11 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

NB:-

  • አሸናፊው ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) 15% (አስራ አምስት ፐርሰንት) የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ፤ ተሽከርካሪዎቹን ሳያዩ የሚጫረቱ ተጫራቾች ቅ/ጽ/ቤቱም ሆነ አክሽን ኢትዮጵያ አ.ማ ሀላፊነቱን አይወስድም።
  • የሻንሲ እና የሞተር ቁጥር የተመታ ተሽከርካሪ ገዝተው መንገድ ትራንስፖርት ሰሌዳ ቁጥር ሲያወጡ መሸጥ እና መለወጥ የማይችሉ እና ቀይ ምልክት ያለው ሰሌዳ በመስጠት በመንገድ ትራንስፖርት በኩል መስተናገድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት

Summary
Customs Commission Jigjiga Branch auctions various contraband vehicles on the Auction Ethiopia app. Any Ethiopian with a residence ID may bid. Vehicles with altered chassis or engine numbers get restricted plates and cannot be resold.
Save Tender
Report a problem with this tender