Tender Detail

Tender Details

  • Company መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር
  • Address አዲስ አበባ ከተማ ወረዳ 03 በተለምዶ አያት ኮንዶሚኒየም ከጠበል መድኃኒአለም ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0930796413
  • Website
  • Deadline03 Dec 2026, 10:30 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Price1000(አንድ ሺህ ብር)
  • Bid Securityየሚገዙበት ዋጋ 10% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ
  • opening dateበ15ኛው ቀን 5:00 ሰዓት
  • Sector Rent , Vehicle Rent , Sales , Disposal Sale

መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር በቅጥር ግቢው የሚገኙ አዳዲስ የኤሌክትሪክ (BYD-E2) እና ሌሎች የተለያዩ ሞዴል ያላቸው በጠቅላላው 12 ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ያወጣው ማስታወቂያ (የጨረታ ሰነድ ቁጥር 133)።

መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር

Add to calendar Google Calendar Download .ics

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ሰነድ ቁጥር 133

መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር በቅጥር ግቢው ውስጥ የሚገኙትን አዳዲስ የኤሌክትሪክ (BYD-E2) እና ሌሎች የተለያዩ ሞዴል ያላቸውን፣ በጠቅላላው 12 ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም ተወዳድሮ መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች አዲስ አበባ ከተማ፣ ለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03፣ (በተለምዶ አያት ኮንዶሚኒየም፣ ከጠበል መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት) በሚገኘው በማዕከሉ ዋና መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ተሽከርካሪዎች በሚገኙበት ቦታ በመገኘት ከተመለከቱ በኋላ በማዕከሉ ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ክፍል ድረስ በመምጣት ብር 1000.00 (አንድ ሺህ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ። የጨረታ ሰነዱ ለሽያጭ የተዘጋጁትን ተሽከርካሪዎች ዝርዝር የያዘ ሲሆን ተሽከርካሪዎቹን እየተዘዋወሩ ከተመለከቱ በኋላ በሠነዱ ላይ በሠሌዳ ቁጥራቸው እና በቻንሲ ቁጥራቸው አንፃር ባለው ክፍት ቦታ የሚገዙበትን ዋጋ በመሙላት እና ለመግዛት ያስገቡትን ዋጋ 10% ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ጋር በማያያዝ ካሸጉ በኋላ የጠቅላላ አገልግሎት ክፍል ድረስ በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 14 ቀን አየር ላይ ቆይቶ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4:30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ5:00 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን የሚከፈትበት ቀን እሁድ ወይም ብሔራዊ በዓል ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።

ማሳሰቢያ

ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09-36-91-91-91/09-30-79-64-13 ወይንም 09-75-26-41-59 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር

Summary
Mekedonia Humanitarian Association sells 12 used vehicles, including new electric BYD-E2 cars and other models, at its head office compound in Lemi Kura sub-city (Ayat), Addis Ababa, by tender. Open to any interested buyer after viewing the vehicles.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender