Tender Detail

Tender Details

  • Company በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251112730852
  • Websitehttps://www.fsc.gov.et/
  • Deadline22 Dec 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየመነሻ ግምቱ 1/4ኛ ብር 647,394.25 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O
  • opening dateምዝገባው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ሐራጁ ይካሄዳል
  • Sector Foreclosure , House and Building , House and Building Maintenance , Sales

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት በፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሰረት በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 02 የሚገኝ የቤት ቁጥር 499 ቤትና ይዞታ ታህሳስ 13 ቀን 2019 ዓ.ም በድጋሚ በሐራጅ ለመሸጥ ያወጣው ማስታወቂያ።

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት

Add to calendar Google Calendar Download .ics

ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍ/ባለመብት የምስራች ሱራፌል እና በፍ/ባለዕዳ እነ መሰረት አሰፋ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ 250214 08/08/2017 ዓም እና መ/ቁ 265663 በ24/10/17 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 02 የሚገኝ ቤት እና ይዞታ የካርታ ቁጥር አ/05/41/7001/00/00 በአቶ ገርባ ደመቀ ስም የተመዘገበ የቤት ቁጥር 499 ጠቅላላ በፐሮፖርሽን የሚደርሰው የቦታ ስፋት 49ካ/ሜ ይዞታው የሰፈር መንገድ የሚነካው ሲሆን 0.59 ካ/ሜ ቤቱ ያረፈበትን የሚቀርጠው ሆኖ ቤቱ በጋራ ግቢ ውስጥ የሚገኝ ሆኖ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ 2,589,577 (ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ሰማንያ ዘጠኝ ሺህ አምስት መቶ ሰባ ሰባት) ሆኖ የትራክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ የተያዘ ቢሆንም በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል። ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.265663 በቀን 30/02/2019 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በድጋሚ ሐራጅ ጨረታ ሆኖ 1/4ኛ ብር 647,394.25 (ስድስት መቶ አርባ ሰባት ሺህ ሶስት መቶ ዘጠና አራት ሺህ) በማስያዝ መሳተፍ የሚቻል ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ታህሳስ 13 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 4:00 ሰዓት ተጀምሮ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጠም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት። በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን ፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን። ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

በፌ/ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

Summary
The Federal Courts Judgment Execution Office re-auctions, by court order, a house (no. 499) in a shared compound in Arada sub-city Woreda 02, Addis Ababa, after the first auction drew no bidders. The buyer pays transaction tax. Open to the public.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender