የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ ለብሄራዊ የአቮካዶ ፕሮግራም አገልግሎት የአቮካዶ ችግኝ ማፍያ ባለ 20 ፕላስቲክ እና የእርሻ መሳሪያ (ጋሪ መግረዣ መጋዝ፣ መከተቢያ ሰንጢና መግረዣ መቀስ) በ2 ሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ያወጣው ማስታወቂያ።
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ የብሄራዊ የአቮካዶ ፕሮግራም አገልግሎት የሚውል ሎት 01 የአቮካዶ የችግኝ ማፍያ ፕላስቲክ ባለ 20፣ ሎት 02 የእርሻ መሳሪያ ጋሪ መግረዣ መጋዝ መከተቢያ ሰንጢ እና መግረዣ መቀስ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል። ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራች ድርጅቶች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- በዘርፉ የተሰማሩ እና በዘመኑ መታደሱን የሚገልፅ ንግድ ፈቃድ እንዲሁም ግብር የከፈሉበትን ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፡ እና የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ወይም በኢጂፒ የተመዘገበ፣
- የግዥው መጠን ብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከኦርጅናሉ ጋር በማገናዘብ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚገዙ የአቮካዶ ችግኝ ማፍያ ፕላስቲክ እና የእርሻ መሳሪያ ግዥ ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን እና መቅረብ ያለባቸው አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 21 ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ብር ጠቅላላ የዕቃ ዋጋ ብር በቁጥር ሎት 01 የአቮካዶ የችግኝ ማፍያ ፕላስቲክ ባለ 20 ብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺ ብር/ ሎት 02 ለእርሻ መሳሪያ ጋሪ መግረዣ መጋዝ እና መከተቢያ ሰንጢ እና መግረዣ መቀስ ብር 500,000.00/አምስት መቶ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (CPO) እና በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከቴክኒካል ሰነዱ ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው። ማንኛውም ተጫራች የጨረታ የመወዳደሪያ/ ሃሳቡን የቴክኒካል ሰነዱን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን ዋና እና ቅጅ ለየብቻው እና የፋይናንሻል ሰነዱን ዋና እና ቅጅ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ግብርና ቢሮ ግቢ ቢሮ ቁጥር 027 ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም ለተጠየቁት ግዥዎች ናሙናቸውን ከቴክኒካል ሰነዱ ጋር አብረው ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግብርና ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ 11ኛ ቀን ቅዳሜ ና እሁድ ወይንም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4:00 ታሽጎ 4:30 ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 27 ድረስ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 2205849/0583208095/ በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ያለምንም ስርዝ ድልዝ የተሞላ ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ይህ ካልሆነ ሰነዱ ተቀባይነት አይኖረውም።
- በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ
Summary
Amhara Region Bureau of Agriculture buys, for the national avocado program, size-20 plastic bags for avocado seedlings and farm tools (pruning saws, grafting knives and pruning shears) in 2 lots. Suppliers with a renewed licence, TIN and supplier or eGP registration may bid.
