የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት በደብረ ማርቆስ፣ በደብረ ብርሃን፣ በኮምቦልቻና በደብረ ታቦር ቅርንጫፎች ስር የሚገኙ የቁም ደን (ባህር ዛፍ፣ ፈረንጅ ፅድ፣ ግራር) እና የተመረተ የፈ/ፅድ ጣውላ ምርቶችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ያወጣው ማስታወቂያ።
የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት ባሕር ዳር
የቁም ደን እና ጣውላ ምርት ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት በደ/ማርቆስ ቅ/ጽ/ቤት ምስ/ጎጃም ዞን ጎንቻ ሲሶ እኔሴ ወረዳ ቀበሌ 01 ምጣድ ዱር መንግስት ደን ውስጥ 6545.6063 ሜ/ኩብ የፈረንጅ ፅድ፣843.8907 ሜ/ኩብ ነጭ ባህርዛፍ፣ 20.4782 ሜ/ኩብ ቀይ ባህርዛፍ፣ 9.9408 ሜ/ኩብ የፈ/ግራር በድምሩ 7,419.9159 ሜ/ኩብ ቁም ደን እና የራባ የመንግስት ደን ውስጥ 416.8642 ሜ/ኩብ የፈረንጅ ፅድ ጣውላ፤በደ/ብርሃን ቅ/ጽ/ቤት ሰ/ሸዋ ዞን ጥርማ በር ወረዳ ደብረ ማዓዛ ቀበሌ ደብረ ማዓዛ የመንግስት ደን ውስጥ 6020.72 ሜ/ኩብ ነጭ ባህርዛፍ ቁም ደን እና ኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት ደ/ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ ቀበሌ 07፣01 እና 04 ጠንገና ቁሰሮ የመንግስት ደን ውስጥ 1508.49 ሜ/ኩብ ነጭ ባህርዛፍና 1022.79 ሜ/ኩብ የፈረንጅ ፅድ በድምሩ 2531.28 ሜ/ኩብ ቁም ደን፤ ደ/ታቦር እንጨት መሰንጠቂያ ላይ የሚገኝ 87.14 ሜ/ኩብ የፈ/ጽድ ጣውላ እና እንጅባራ ከተማ እንጨት መሰንጠቂያ የተመረተ 119.01 ሜ/ኩብ የፈ/ጽድ ጣውላ ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች:-
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- የሽያጭ መጠን 200,000.00/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተእታ VAT ምዝገባ የምስክር ወረቀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ለጨረታ የቀረበውን ቁም ደንና የጣውላ ምርት /ምርቶች/ ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት በቦታው ተገኝተው ማየት ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የስራ ቀናት ውስጥ ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት ባሕርዳር ቀበሌ 14 አዲሱ መናኸሪያ ጀርባ እንስሳት ማዳቀያ ግቢ ዉስጥ ከኢንተርፕራይዙ ቢሮ ቁጥር 06 እና በሁሉም ቅ/ጽ/ቤቶች የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለመግዛት የሚፈልጉትን ምርት ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ/CPO/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን ቁም ደን /ጣውላ/ በኦሪጅናል ዋጋ መሙያ ቅፅ የሚገዙበትን ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ፣ ስምና አድራሻቸውን በመፃፍ ፈርመው በመሙያው ሰነዱ ላይ ማህተም በማስቀመጥ የታሸገውን የጨረታ ፖስታ በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06፣ደ/ብርሃንና ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች «የቁም ደን እና የጣውላ ምርት ሽያጭ ማስታወቂያ» ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 የስራ ቀናት (ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ) እስከ መጨረሻው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ቀን በ4:00 ሰዓት ላይ ሳጥኑ ታሽጎ በ4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ይሁን እንጂ ተጫራቾች ባይገኙም ይከፈታል።
- ተጫራቾች የሚሞሉት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ 15% ተእታን አይጨምርም። ሆኖም አሸናፊው ባሸነፈበት ዋጋ ላይ 15% ተእታን ጨምሮ ይከፍላል።
- ተጫራቾች ቁም ደኑን በተመለከተ ቅልቅል ደን ተብሎ የቀረበውን ሁሉንም ከፍልፋይ መሙላት ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የጣውላ ምርቱን የሚፈልጉትን ሎት ብቻ መጫረት የሚችሉ መሆኑንና የተወዳደሩበትን ሎት የጣውላ ምርት ሁሉንም ምርት ክፍያ ፈፅመው ማንሳት አለባቸው።
- በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ:- በስልክ ቁጥር ባ/ዳር 0582263095፣ ደ/ታቦር 0584410306፣ ደ/ብርሃን 0116375017፣ እንጅባራ 0582270485፣ ደ/ማርቆስ 0588719004፣ ኮምቦልቻ 0914716636 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት /ባሕር ዳር/
Summary
Amhara Forest Enterprise sells standing forest (eucalyptus, cypress, acacia) in state forests under its Debre Markos, Debre Birhan and Kombolcha branches, plus sawn cypress timber at Debre Tabor and Injibara, as-is by open tender. Licensed traders with TIN may bid.
