በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጎፋ ዞን የደምባ ጎፋ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሮኒክስ፣ የጽህፈት መሣሪያና የፋብሪካ ዕቃዎችን ለ2019 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ያወጣው የ1ኛ ዙር ጨረታ ማስታወቂያ።
በጎፋ ዞን የደምባ ጎፋ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት
1ኛ ዙር የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ/ኢ/ክ/መንግሥት በጎፋ ዞን የደምባ ጎፋ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል በ2019 በጀት ዓመት የኤሌክትሮኒክስ፣ የጽህፈት መሣሪያና የፋብሪካ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የተጫራቾች መስፈርቶች:-
- በዘርፉ በ2018 ዓ/ም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- የዘርፉ ንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- በመንግስት ግዥ አቅራቢነት የተመዘገበ
- የግዥ ኤጀንሲ ጨረታ ላይ እንዳይሳተፍ ዕገዳ ያልተጣለበት
- ግብር የከፈሉበት ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል
የተጫራቾች ግዴታዎች:-
- ከተራ ቁጥር 1 እስከ 6 ያሉ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈልና ሠነድ በመግዛት ለዚህ በተዘጋጀው ጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት ዕቃዉ በራሱ ወጭ እስከ ደምባ ጎፋ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ግቢ ማቅረብ አለበት
- ጥራትና ደረጃውን የጠበቀ ዕቃ ማቅረብ አለበት።
- ናሙና የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን ለመ/ቤቱ በቅድሚያ ማቅረብ አለበት
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000.00/አምስት ሽህ ብር በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ እውቅና ካለው ባንክ ማስያዝ አለበት።
- የውል ማስከበሪያ ጠቅላላ የግዥ ዋጋ 10% በጥሬ ገንዘብ ወይም የባንክ cpo ማቅረብ የሚችል፤
- አሸናፊ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ጊዜ ውስጥ ቀርቦ ውል መግባት አለበት።
- የወቅቱን የገበያ ዋጋ ያላገናዘበ የጨረታ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም
- የጨረታ ሠነድ ከደምባ ጎፋ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በመግዛት የገዙትን ሠነድ በመሙላት የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ ተደርጎበት ዋናውና ኮፒው በሁለት ሉብቻ ለዚህ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀንና ዓ/ም ጀምሮ 15 የሥራ ቀናት ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ የሚከፈተዉ ከታሸገበት 30 ደቂቃ በኋላ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል። ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ያለመገኘት የጨረታዉን ሰነድ የመክፈት ሂደቱን አያስተጓጉልም።
ማሳሰቢያ
- በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ማንኛውም ተጫራች የሚፈልገውን ዕቃ ዋጋ የማቅረቢያ ሠነድ የተጠቀሰውን ዕቃ ሙሉ በሙሉ መሙላት።
በጎፋ ዞን የደምባ ጎፋ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት
Summary
Demba Gofa Woreda Finance and Plan Office (Gofa Zone, South Ethiopia) buys electronics, stationery and factory goods for its sector offices by open tender. Bidders need a renewed licence, VAT and TIN registration, supplier registration and tax clearance.
