ልህቀት የዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን የሸራተን ወንበር ግዥ
Lihiket Design & Supervision Corporation Bahir Dar (የልህቀት የዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን ባህርዳር)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ሠነድ ቁጥር:- ልዲቁኮ - 09/2019
ልህቀት የዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን ሸራተን ወንበር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው መወዳደር ይችላል።
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ባህር ዳር በግዥና ንብ/አስ/ቡድን የስራ ክፍል ቢሮ ቁጥር 008 በመቅረብ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ ጨረታ መዝጊያው ቀን ድረስ መግዛት ይቻላል።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 8:30 ሰዓት ላይ ለመገኘት የቻሉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዳቸውን፣ የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 2% በሲፒኦ ወይም እንደተጠየቀ ወዲያውኑ በሚከፈል የባንክ ጋራንቲ በፖስታ አሽገው እስከ ጨረታ መዝጊያው ቀንና ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 008 ማቅረብ ወይም ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ:- ስልክ ቁጥር 058-218-02-73 ሞባይል 09-18-08-55-89 በመደወል ወይም በፋክስ ቁጥር 058-218-05-50 በመላክ መጠየቅ ይቻላል።
ልህቀት የዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን
ባህርዳር, ኢትዮጵያ
✨ messages.ai_summary
Lihiket Design and Supervision Corporation (Bahir Dar) invites bids for the supply of Sheraton chairs. Open bid.
