የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ያልተከፈለ የጡረታ መዋጮ ዕዳ ለማስከፈል የሦስት ድርጅቶችን ተሽከርካሪዎች/ማሽነሪዎች በምዕራብ ሐረርጌ ባዴሳ ከተማ እና በአዲስ አበባ በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ያወጣው ማስታወቂያ።
የግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር
በግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የጡረታ መዋጮ ዕዳ ለማስከበር የወጣ የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
ስማቸው ከዚህ በታች የተመለከቱት ድርጅቶች ከሠራኛው መደበኛ የወር ደመወዝ ላይ ተገቢውን የጡረታ መዋጮ ቀንሰው እና የድርጅቱን ድርሻ መዋጮ ጨምረው ለግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ ፈንድ ገቢ ማድረግ ባለመቻላቸው የግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር በአዋጅ ቁጥር 1268/2014 በተሠጠው ስልጣን መሠረት የድርጅቶቹን ሃብት በግልጽ ጨረታ በመሸጥ ውዝፍ ጡረታ መዋጮ ዕዳውን እንዲሰበሰብ ተወስኗል።በዚሁ መሠረት
| ተራ ቁጥር | ውዝፍ የጡረታ መዋጮ ዕዳው የሚፈለግበት ድርጅት ስም | ከድርጅቱ የሚፈለገው የጡረታ መዋጮ ዕዳ መጠን | የተሽከርካሪው ወይም የማሽነሪው ሠሌዳ ቁጥር | የድርጅቱ ሃብት የሚገኝበት አድራሻ | የጨረታ መነሻ ዋጋ |
|---|---|---|---|---|---|
| 1 | ኤል አስብ ጀኔራል ትራንስፖርት ኤንድ ኮንስትራክሽን ኢስቴብ | 27,110,777.29 | የሠሌዳ ቁጥር ሥክ-cs-0636 | በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምእራብ ሐረርጌ ዞን ባዴሳ ከተማ | 37,082,909.90 |
| 2 | ሩሜ አግሮ ኢንደስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማ | 7,230,029.01 | የሠሌዳ ቁጥር አአ-03-A22792 | አዲስ አበባ የግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ዋና መስሪያ ቤት | 757,336.71 |
| 3 | ኤልሻዳይ ሪሊፍ ኤንድ ዴቨሎፕመንት አሶሴሽን | 6,595,375.93 | የሠሌዳ ቁጥር አአ-05-02606 | አዲስ አበባ የግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ዋና መስሪያ ቤት | 683,948.25 |
- ስለሀብቱ አሻሻጥ ከአስተዳደሩ የግዥ ዳይሬክቶሬት ወይም ከህግ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት መረጃ ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ከግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ብር 200.00 በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ንብረቱን የሚገዙበትን ዋጋ በግልጽ በማስፈር በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው አድራሻው ለግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ዋና መ/ቤት በማለት አስፍረው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የስራ ቀናት ጠዋት ከ2:00 እስከ 6:00 ሠዓት እንዲሁም ከሠአት ከ7:00 እስከ 11:00 ሠዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው የግልጽ ጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች በቅድሚያ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/10ኛውን በጥሬ ገንዘብ ወይም ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ አለባቸው።
- ጨረታው በ16ኛው የስራ ቀን ጠዋት 4:00 ሠዓት ተዘግቶ በ4:15 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስተዳደሩ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል። የመክፈቻው ቀን የእረፍት ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት የሚከፈት ይሆናል።
- ተጫራቾች ተሽከርካሪዎቹ ወይም ማሽነሪዎቹን በግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ዋና መ/ቤት በሚያመቻቸው ፕሮግራም በአካል በመገኘት መመልከት ይችላሉ።
- አሸናፊው ያስያዘው ገንዘብ ከሻጭው ዋጋ ጋር ታስቦ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ አጠናቆ በመክፈል ሃብቱን መረከብ አለበት።
- የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀናት ውስጥ አጠናቆ የማይከፍል ከሆነ ለጨረታው በዋስትና ያስያዘው ገንዘብ ለአስተዳደሩ ገቢ ሆኖ የጨረታው አሸናፊነቱ ይሠረዛል።
- ከሽያጩ ጋር በተያያዘ የሚከፈሉ ግብርና ታክሶች፣ የስም ማዛወሪያ እንዲሁም ሌሎች ማናቸውም ህጋዊ ወጪዎች በገዢ ይሸፈናሉ።
- አስተዳደሩ ስለሀብቱ አሻሻጥ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ መገናኛ ቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር ፊት ለፊት
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111570333
የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር
✨ messages.ai_summary
The Private Organization Employees Social Security Administration sells by open tender three vehicles/machines seized from firms with unpaid pension contributions, one in Bedessa town, West Hararghe, and two at its Addis Ababa head office. Open to all bidders; inspection arranged.
