Tender Detail

Tender Details

  • Company በደ/ምዕ/ኢት/ህ/ክ/መ በቤንች ሸኮ ዞን የሚዛን አማን ከተማ አስ/ር የመጀ/ደረጃ ፍ/ቤት
  • Address , Phone: 0928287698
  • Website
  • Deadline29 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Priceበነጻ
  • Bid Securityየጠቅላላ ዋጋ 2% (CPO)
  • opening dateበዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት
  • Categories Stationery Materials , Cloth And Shoes

የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የጽህፈት መሳሪያ፣ የህግ መጻሕፍትና የዳኞች ካባ ግዥ

በደ/ምዕ/ኢት/ህ/ክ/መ በቤንች ሸኮ ዞን የሚዛን አማን ከተማ አስ/ር የመጀ/ደረጃ ፍ/ቤት


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በደ/ምዕ/ኢ.ት/ህ/ክ/መ/በቤንች ሸኮ ዞን የሚዛን አማን ከተማ አስ/ር የመጀ/ደ/ፍ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚሆን የጽህፈት መሳሪያ፤የተለያዩ የህግ መጽሃፍቶች፤የደንብ ልብስ (የዳኞች ካባ) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁም መሰረት:-

  1. በዘርፉ የተሰማሩበትን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
  3. በዕቃ አገልግሎት አቅራቢነት የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፤
  5. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ የያዘ ሰነድ(Specification)ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ እስከ 15(አስራ አምስት) ተከታታይ ቀን ዘወትር በስራ ሰዓት በሚ/አ/ከ/አስ/ር የመጀ/ደ/ፍ/ቤት የግዥ ፋይ/ን/አስ/ር ቢሮ ቁጥር 8 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን በነጻ መውሰድ ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ጠቅላላ የዕቃ ዋጋ 2% በባንክ በተመሰከረ ቼክ(CPO)ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
  7. ተጫራቾች ዋጋቸውን ሞልተው የሚያቀርቡት በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተቀመጠው የዕቃዎችና ተያያዥ አገልግሎት የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ በሚለው የዕቃዎች ዝርዝር መሰረት ብቻ ይሆናል።
  8. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውን በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ሞልተው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም አርፎበትና ተፈርሞበት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  9. የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀኖች ክፍት ሆኖ ከቆየ በኋላ በ16ተኛ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  10. የጨረታ መከፈቻ ቀን የበዓል ቀን ወይም ቅዳሜና እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ላይ ይከፈታል።
  11. የተጫራቾች ተሟልቶ አለመገኘት የጨረታውን አከፋፈት ስነ-ስርዓቱን አያስተጓጉልም።
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዙ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  13. ጨረታውን ያሸነፈ ያሸነፋቸውን ዕቃዎችን ለሚ/አ/ከተ/አስ/ር የመጀ/ደ/ፍ/ቤት ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር:- 0928287698 እና 0917151712 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

በቤንች ሸኮ ዞን የሚዛን አማን ከተማ አስ/ር የመጀ/ደረጃ ፍ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Mizan Aman Town First Instance Court (Bench Sheko Zone) seeks suppliers of stationery, various law books and judges' robes. Open bid.
Save Tender