ዋቢ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒዮን የአፈር ማዳበሪያ ማጓጓዝ አገልግሎት
የዋቢ ሁለገብ የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ማኀራት ዩኒየን ኃ/የተወሰነ
የአፈር ማዳበሪ ለማጓጓዝ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በሰቆጣ ከተማ የሚገኘው ዋቢ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒዮን /ኃ/የተወሰነ:: ከሰቆጣ ሳቃ 1834 ኩ/ል ከሰቆጣ ኒየርአቹ 1224.5 ኩ/ል እና ከሰቆጣ ፃታ 200 ኩ/ል በድምሩ 3258.5 ኩ/ል በግልጽ ጨረታ በማወዳደር የአፈር ማዳበሪያ ማጓጓዝ ይፈልጋል:: በመሆኑም መስፈርቱን የሚያሟሉ ትራንስፖርተሮች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል ::
- በዘመኑ የ2019 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብርን የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ (የምትችል)
- ከሚጓጓዘው የትራንስፖርት (የጭነት) አገልግሎትና የትራንስፖርት ፍቃድ) ጋር የተዛመደ ንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው የግብር ከፍይነት ምስክር ወረቀት (Tax payer identification Number) እንዲሁም ሌሎች ለጨረታው የሚጠቅሙ ማስረጃዎችን የተገናዘበ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም የወዛደር የመጫኛና ማውረጃ በትራንስፖርተሩ የሚሸፈን ሆኖ መኪናው የመጫን አቅም ከ200 ኩ/ል እስከ 220 ኩ/ል በአንድ ጊዜ ማንሳት የሚችል መሆን አለበት ::
- ተጫራቾች የሚገዛውን የትራንስፖርት አገልግሎትና የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 / ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ የጨረታ ሰነድ ሰቆጣ ከተማ ወይብል ማርያም አጠገብ ከሚገኘው ዋቢ ዩኒዮን ቢሮ ቁጥር 1 በመምጣት መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን ::
- ተጫራቾች በሌላ ዋጋ ተመስርቶ መወዳደር የማይቻል መሆኑንና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው አሸናፊ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 2 ቀናት እንዲሁም የውል ማስከበሪያ ዋስትናው ውል ከተፍጸመበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 30 ቀናት ፀንቶ ሊቆይ የሚችል መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል ::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በተፈቀደላቸው በታወቁ ባንኮች ዋስትና (C.P.O) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (C.P.O) ወይም በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ዋቢ ዩኒዮን ገቢ በማድረግ/ዋናውን የገቢ ደረሰኝ / ከማወዳደሪያ ሃሳብ ጋር አብሮ ማስገባት ሲኖርባቸው በጨረታ ሰነዱ ከተቀመጠው ዝርዝር መግለጫ ውጭ መጨመርም ሆነ መቀነስ አይፈቀድም::
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ 5 /አምስት/ ተከታታይ የስራ ቀናት ሰነዱን በመግዛት የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ሰቆጣ ከተማ ወይብላ ማሪያም በስተጀርባ ከሚገኘው ዋቢ /ሁለገብ /የገ/ህ/ስ/ማ/ኃላፊነቱ የተወሰነ ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በ6ኛ ቀን /ስድስተኛው/ ቀን /3:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል ::
- የጨረታ ሰነዱ የሚከፈተው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎች/ በተገኙበት ዋቢ ሁለገብ /የገ/ህ/ስ/ማ ሃላፊነቱ የተወሰነ ጨረታው ከወጣበት ቀን ለተከታታይ 5 /አምስት/ ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ፀንቶ ቆይቶ በ /በአስራአንደኛው/ ቀን ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪል/ በተገኙበት ከጥዋቱ 3:00 ሰዓት ታሽጎ 3:30 ጨረታው ይከፈታል::
- ተጫራቾች የጨረታ ማወዳደሪያ ሃሳባቸውን ለማሻሻል ወይንም ከጨረታው ለመውጣት የፈለጉ እንደሆነ የጨረታ ማወዳደሪያ ሃሳብ ለማቅረብ ከተሰጣቸው 3 ቀን /ሶስት ቀን /በፊት በፅሁፍ ሊያሳውቁ ይገባል ::
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::ይህም ሲባል ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ኃላፊነት የማይወስድ መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ዋግ ኽምራ ብሄረሰብ ዋቢ ሁለገብ የገ/ህ/ስ/ማህበር ኃላፊነቱ የተወሰነ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0334401173/0941821789/0933214815 በመደወል ማግኘት ይችላሉ::
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር
✨ messages.ai_summary
Wabi Multipurpose Farmers Cooperative Union in Sekota, Wag Hemra, Amhara, seeks transporters to carry 3258.5 quintals of fertilizer from Sekota to Saka, Niyerachu and Tsata, with trucks of 200-220 quintal capacity. Open bid.
