Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address አዋሽ ፡ አፋር ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09-13-97-49-27
  • Website
  • Deadline20 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • CountryEthiopia
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityግልጽ ጨረታ የእቃ ኮድ 5%፤ ሐራጅ ለእቃ ኮድ ብር 100,000 (CPO)
  • opening dateየሐራጅ ጨረታ በ11/03/2019 ዓ/ም 11:00 ሰዓት (በአክሽን ኢትዮጵያ)
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale

የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተወረሱ የኮንትሮባንድ ልዩ ልዩ ዕቃዎችና ተሽከርካሪ የግልጽና የሐራጅ ሽያጭ

የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በ11/03/2019 ዓ/ም በግልጽና በሐራጅ ጨረታ በአክሽን ኢትዮጵያ(auction ethiopia) መተግበሪያ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች መተግበሪያውን ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር auction Ethiopia ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ በመመዝገብና የጨረታ ሰነዱን በማየት፣ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በሟሟላት በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን፣ የእቃዎችን ሳምፕልም ከአክሽን ኢትዮጵያ ድህረ-ገጽ(auction ethiopia page) ወይም አዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ወይም በቴሌግራም እንዲላክሎት በማድረግ ማየት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን::

የጨረታ መስፈርቶች:-

  1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ ተጫራቾች በጨረታ በሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፍኬት፣የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለ መሆኑ ክሊራንስ (Clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ለታክስ ማዕከሉ ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በሲስተም አታች ማድረግ ይኖርባቸዋል::
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀን በ11/03/2019 ዓ/ም ከአክሽን ኢትዮጵያ ድህረ-ገጽ(auction ethiopia page) ማየት ይችላሉ::
  3. ለግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (cpo) የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5 በመቶ እንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩበት እቃ ኮድ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ አሰርተው በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም በማስያዝ በሲስተም አታች ማድረግ ይኖርባቸዋል::
ተ.ቁአጫራች ቅ/ጽ/ቤትየጨረታው ዓይነትለጨረታ የቀረቡ እቃዎችየዕቃዎች መመልከቻ ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከየጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት
1አዋሽ ጉ/ቅ/ጽ/ቤትግልጽ ጨረታ እና በሐራጅጫማዎች፣ አልባሳት፣ የመኪና መለዋወጫ፣ የሞባይል ቀፎና አሰሰሪ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ምግብ ነክ፣ የስፖርት እቃዎች፣የእጅ ሰዓት፣ ኮስሞቲክስ፣ መነፅር፣ ጌጣ ጌጥ፣ የሳሙና ፋብሪካ አካል ማሽነሪ ተሽከርካሪ እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎችለግልጽና ለሐራጅ ጨረታበ11/03/2019 ዓ/ም እስከ ከሰዓት 9:45ለግልጽ ጨረታ መዝጊያ ጊዜ በ11/03/2019 ዓ/ም እስከ ከሰዓት 10:00፡ሲሆን የሐራጅ ጨረታ የመጀመሪያ ጊዜ በ11/03/2019 በ11/03/2019 ዓ/ም 11:00 ሰዓት ይሆናል::
  1. የጨረታው መክፈቻ ሰዓት እና ቀንን ከአክሽን ኢትዮጵያ ድህረ-ገጽ(auction ethiopia page) በማየት የጨረታው ሂደት ተጀምሮ ከማለቁ በፊት ዋጋ መስጠት ይችላሉ::
  2. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (c.p.o) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል::
  3. ከአሸፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ3 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን በመረከብ ከመጋዝን ማውጣት ይኖርበታል::
  4. ከላይ በተ.ቁ.7 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ የከፈሉት ዋጋ ለኮሚሽኑ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል::
  5. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Awash Customs Branch Office is selling confiscated contraband goods, including shoes, clothing, vehicle spare parts, mobile phones, electronics, food items, cosmetics, soap factory machinery and a vehicle, by open bid and auction on the Auction Ethiopia app.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender