Tender Detail

Tender Details

  • Company በኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ አሰላ ካምፓስ
  • Address Oromia Ethiopia, Phone: 0930107417 /0911742980/
  • Website
  • Deadline26 Sep 2026, 9:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price500.00 /አምስት መቶ/ ብር
  • opening dateበዚሁ ዕለት ጠዋት በ3፡30
  • Categories Food And Beverage , Catering And Cafeteria Services , Food Items And Drinks

በኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ አሰላ ካምፓስ በ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት ለካምፓሱ ሰልጣኞች አገልግሎት የሚውሉ ልዩ ልዩ የምግብ ግብዓቶችንና የበሰሉ ምግቦችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ አሰላ ካምፓስ በ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት ለካምፓሱ ሰልጣኞች አገልግሎት የሚውሉ ልዩ ልዩ የምግብ ግብዓቶችንና የበሰሉ ምግቦችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም፡-

  1. ለተጠየቁት ምግቦች የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆናችሁ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላችሁ እና በፈዴራል፣ በክልል ወይም በዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ወይም በግዢዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የአቅራቢነት የምስከር ወረቀት ያላችሁ ዋናውንና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በካምፓሱ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 1 ድረስ በመቅረብ ሰነዱን 500.00 /አምስት መቶ/ ብር ባንክ ገቢ በመድረግ በግዥ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመክፈላቸው እና ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በተከታታይ እስከ 16ኛው የሥራ ቀናት ጠዋት 3:00 ሰዓት ማቅረብ እና ሳጥን መስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ጠዋት በ3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በካምፓሱ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የተወቀ ባንክ በከፍያ ማዘዣ(C.P.O.) ለእህል እና ፍራፍሬ ብር 100,000.00/መቶ ሺህ/ ፡ስጋ፡ዳቦ: ማገዶ ብር 30,000.00/ ሠላሳ ሺህ/ በካምፓሱ ስም በመስያዝ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  5. አሸናፊው ተጫራች አስተማማኝ የሆነ የምግብ ክምችት ያለውና ምግቦቹንና የምግብ ግብዓቶችን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ አሰላ ከተማ በሚገኘው በካምፓሱ ግቢ ድረስ አምጥቶ ካምፓሱ በሚሰጠው ፕሮግራም መሰረት ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
  6. ካምፓሱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0930107417 /0911742980/ ይጠይቁ፡፡

በኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ አሰላ ካምፓስ

✨ messages.ai_summary
Oromia State University Asella Campus seeks suppliers for various food ingredients and cooked meals for its trainees. Bidders need a renewed business license, VAT registration, TIN, and a supplier certificate. The winner must have reliable food stock and deliver to campus at their own cost.
Save Tender