የምስራቅ ዕዝ ግልፅ ጨረታ ቁጥር 01/2018 ዓ.ም በሀገር መከላከያ ሚ/ር በምስራቅ ዕዝ የ304ኛ ኮርጠ/መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት ለኮርና ለከ/ጦር አገልግሎት የሚውሉ - 1. የጽሕፈት መሣሪያ እና የትምህርትና ሥልጠና መርጃ እቃዎች 2. የፅዳት እቃዎች 3. የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች 4. የጀነሬተር ፓምፕ መለዋወጫ እቃዎች በዘርፉ ከተሰማሩ ሕጋዊ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡