መሪ ቦሌ ሸማቾች ኃ/የተ/የኅ/ሥ/ማኅበር በአዋጅ ቁጥር 985/2009 መሠረት ለአባላቱና ለሌሎች አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል።በመሆኑም የ2017 በጀት ዓመትን የማኅበሩን ሂሳብ በውጭ ኦዲተሮች ለማስመርመር በኢትዮጵያ አካውንቲንግና ኦዲት ቦርድ /AABE/እውቅና የተሰጣቸውን የኦዲት ተቋማትን/ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።