መሪ ቦሌ ሸማቾች ኃ/የተ/የኅ/ሥ/ማኅበር በአዋጅ ቁጥር 985/2009 መሠረት ለአባላቱና ለሌሎች አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል።በመሆኑም የ2017 በጀት ዓመትን የማኅበሩን ሂሳብ በውጭ ኦዲተሮች ለማስመርመር በኢትዮጵያ አካውንቲንግና ኦዲት ቦርድ /AABE/እውቅና የተሰጣቸውን የኦዲት ተቋማትን/ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
መሪ ቦሌ የሸማቾች ኃሳፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር
የውጭ ኦዲተር ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
መሪ ቦሌ ሸማቾች ኃ/የተ/የኅ/ሥ/ማኅበር በአዋጅ ቁጥር 985/2009 መሠረት ለአባላቱና ለሌሎች አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል።በመሆኑም የ2017 በጀት ዓመትን የማኅበሩን ሂሳብ በውጭ ኦዲተሮች ለማስመርመር በኢትዮጵያ አካውንቲንግና ኦዲት ቦርድ /AABE/እውቅና የተሰጣቸውን የኦዲት ተቋማትን/ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች/የኦዲት ድርጅቶች እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።
ፍላጎት ያላችሁ የኦዲት ድርጅቶች፡-
1. ቴከኒካል መነሻ ሀሳብ /Technical Proposal
2. የፋይናንስ መነሻ ሀሳብ /Financial Proposal
3. የዘመኑ የታደሰ አግባብ ያለው ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ማስረጃ፣ የአቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት እንዲሁም የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. የጨረታ ሂደቱ የማኅበሩን የግዥ ሂደት የተከተለና በሀገሪቱ የግዥ ሕግ መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል።
5. በኢትዮጵያ አካውንቲንግና ኦዲት ቦርድ / AABE / እውቅና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
6. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል በለሚ ኩራ ከ/ከተማ ወረዳ 10 አስተዳደር ጽ/ቤት አጠገብ ዘወትር በሥራ ሰዓት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታ ዋጋውን 2 በመቶ በሲፒኦ /በሁኔታ ላይያልተመሰረተ / ከፋይናንስ ፖስታ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
8. ለተጫራቾች ቴከኒካል መነሻ ሀሳብ / Financial Proposal / የሚሆናቸውን ዝርዝር ቢጋራ /TOR / የያዘ ሰነድ በማኅበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት መውሰድ ይጠበቅባቸዋል፡፡
9. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 የሥራ ቀናት የሚቆይ ከሰኞ ቅዳሜ 6፡30 ሆኖ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል መነሻ ሀሳብ ሰነዳቸውን ካስገቡ በኋላ በዕለቱ 10ኛው ቀን ከሠዓት በኋላ 11፡30 ላይ ተዘግቶ በማግስቱ ማለትም በ11ኛው የሥራ ቀን ላይ ጠዋት 4፡00 ሰዓት በማህበሩ ዋና ቢሮ የሚከፈት ይሆናል።
10. የጨረታው መከፈቻ ከኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ሠዓት በማኅበሩ ዋና ቢሮ የሚከፈት ይሆናል።
11. ማኅበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. ስለጨረታው ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ከፈለጉ ቀጥሎ ባለው የስልክ ቁጥር፡- 0911 95 49 88 /0913 73 2850 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
መሪ ቦሌ የሸማቾች ኃሳፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር
