በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን ቆጎታ ወረዳ ፋይናንስ ጽሕፈት ቤት በወረዳው ለሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ለ2018 በጀት ዓመት የጽሕፈት መሳሪያ ብር 10,000 /አስር ሺህ/፣ የህንጻ መሳሪያ፣ የውሃ ዕቃዎች ብር 40,000 /አርባ ሺህ/ እና አጠቃላይ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ብር 10,000 /አስር ሺህ/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡