በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን ቆጎታ ወረዳ ፋይናንስ ጽሕፈት ቤት በወረዳው ለሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ለ2018 በጀት ዓመት የጽሕፈት መሳሪያ ብር 10,000 /አስር ሺህ/፣ የህንጻ መሳሪያ፣ የውሃ ዕቃዎች ብር 40,000 /አርባ ሺህ/ እና አጠቃላይ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ብር 10,000 /አስር ሺህ/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን የቆጎታ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 06 /2018
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን ቆጎታ ወረዳ ፋይናንስ ጽሕፈት ቤት በወረዳው ለሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ለ2018 በጀት ዓመት የጽሕፈት መሳሪያ ብር 10,000 /አስር ሺህ/፣ የህንጻ መሳሪያ፣ የውሃ ዕቃዎች ብር 40,000 /አርባ ሺህ/ እና አጠቃላይ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ብር 10,000 /አስር ሺህ/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች
- ተጫራቾች በጋሞ ዞን ቆጎታ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 06 በማምጣት የጨረታ ዝርዝር መረጃ /ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ከፍለው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ አስራ አምስተኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በየሎት ዓይነት መሰረት በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /cpo/ ማስያዝ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የሚወዳደርበት ዕቃ ጥራት፣ ዓይነትና መጠን በትክክል በማጣራት በቀረበው ስፔስፊኪሽን መሰረት ማቅረብ አለበት፡፡
- የሚቀርበው ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ የቀረበው እንደተካተተ ተቆጥሮ ይመዘገባል፡፡
- ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የንግድ ምዘገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ
- ማንኛውም ተጫራች ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በሰነድ ላይ በተገለጸው ስፔስፍኬሽን ሞዴልና ብራንድ መሰረት ብቻ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ አፈጻጸም ወይም ሂደቱ ላይ ቅሬታ ካላቸው በግዥ አዋጁ መሠረት አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው፡፡
- ማንኛውም የጨረታውን ሂደት ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራች ከጨረታ ውጪ ተደርጎ ግዥ ላይ እንዳይሳተፍ ይደረጋል፡፡
- የጨረታ ሰነድ የሚታሸገው ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት በ16ኛ ቀን 8፡00 ሰዓት ሲሆን የሚከፈተው በዕለቱ ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡ ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ዶክመንት ቴክኒካልና ፋይናንሻል ኦርጅናልና ሁለት /2/ ኮፒ እንዲሁም CPO በተለያዩ ፖስታ እድርጎ በእናት ፖስታ አሽጎ እንዲያቀርቡ ይፈለጋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊነት ከተገለፀላቸው በኋላ የውል ማስከበሪያ በአሸነፉበት ከጠቅላላ ዋጋ 5% በማስያዝ ውል መዋዋል ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በራሳቸው ትራንስፖርት የጨረታ አሸናፊ ድርጅት መስሪያ ቤቱ ድረስ ዕቃዎችን ማቅረብ ይኖርበታል።
- የተጫራቾች ያለመኖር የጨረታ ሂደቱን አያስተጓጉልም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቆጎታ ወረዳ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0916853226/ 0916700423 በመደወል መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን የቆጎታ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
