አዋሽ ወይን አ.ማ. በድርጅቱ ግቢ ማለትም ከመካኒሳ አዋሽ ወይን ጠጅ ፍብሪካ በማምረት ሂደት ዉስጥ የሚመረተውን የፍሳሽ ቆሻሻ ከማጠራቀሚያው ጉድጓድ (septic tank) በማንሳት ልደታ በሚገኘው የወይን ጠጅ ፋበሪካችን ውስጥ የፍሳሽ ዉሃ ማከሚያ ፕላንት በመገልበጥ ይሆናል። እንዲሁም ከልደታ ቅርንጫፍ ወደ ታወቀ የስላጅ መድፊያ ቦታ ጭቃውን ፓምፕ በማድረግ መውሰድ ይሆናል። በመሆኑም ይህን ፍላጎቱን ለማሳካት ከ 16,000 ሊትር በላይ ፍሳሽ የሚያመላልስ መኪና፤ ብቁና ተገቢው የስራ ልምድ ያለውና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎች የሚያሟላ ማንኛውንም ተጫራች አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።