Tender Detail

Tender Details

  • Company Awash Wine S.C (አዋሽ ወይን አ.ማ.)
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0918913895
  • Websitehttps://awashwines.com/
  • Deadline26 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-10-26 00:00:00
  • Categories Cleaning & Janitorial , Vehicles Rent

አዋሽ ወይን አ.ማ. በድርጅቱ ግቢ ማለትም ከመካኒሳ አዋሽ ወይን ጠጅ ፍብሪካ በማምረት ሂደት ዉስጥ የሚመረተውን የፍሳሽ ቆሻሻ ከማጠራቀሚያው ጉድጓድ (septic tank) በማንሳት ልደታ በሚገኘው የወይን ጠጅ ፋበሪካችን ውስጥ የፍሳሽ ዉሃ ማከሚያ ፕላንት በመገልበጥ ይሆናል።  እንዲሁም ከልደታ ቅርንጫፍ ወደ ታወቀ የስላጅ መድፊያ ቦታ ጭቃውን ፓምፕ በማድረግ መውሰድ ይሆናል። በመሆኑም ይህን ፍላጎቱን ለማሳካት ከ 16,000 ሊትር በላይ ፍሳሽ የሚያመላልስ መኪና፤ ብቁና ተገቢው የስራ ልምድ ያለውና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎች የሚያሟላ ማንኛውንም ተጫራች አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

Awash Wine S.C (አዋሽ ወይን አ.ማ.)


 

የአዋሽ ወይን አ.ማ.

የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ

 

አዋሽ ወይን አ.ማ. በ1936 ዓ.ም. የተመሰረተ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የወይን ፋብሪካ ሲሆን አዋሽ፣ ጉደር፤ አክሱሚት ከሚላና ገበታ የተባሉ የወይን ምርቶችንና ዳንኪራ የወይን ኮክቴልን በማምረት ለህብረተሰቡ በማቅረብ ይታወቃል።

አዋሽ ወይን አ.ማ. በድርጅቱ ግቢ ማለትም ከመካኒሳ አዋሽ ወይን ጠጅ ፍብሪካ በማምረት ሂደት ዉስጥ የሚመረተውን የፍሳሽ ቆሻሻ ከማጠራቀሚያው ጉድጓድ (septic tank) በማንሳት ልደታ በሚገኘው የወይን ጠጅ ፋበሪካችን ውስጥ የፍሳሽ ዉሃ ማከሚያ ፕላንት በመገልበጥ ይሆናል።  እንዲሁም ከልደታ ቅርንጫፍ ወደ ታወቀ የስላጅ መድፊያ ቦታ ጭቃውን ፓምፕ በማድረግ መውሰድ ይሆናል። በመሆኑም ይህን ፍላጎቱን ለማሳካት ከ 16,000 ሊትር በላይ ፍሳሽ የሚያመላልስ መኪና፤ ብቁና ተገቢው የስራ ልምድ ያለውና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎች የሚያሟላ ማንኛውንም ተጫራች አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

መስፈርቶች

  • የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የግብር መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት፤ እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ህጋዊ ማስረጃዎችን ማቅረብ የሚችል
  • የሚያቀርበው የፍሳሽ መኪና ለስራው ብቁ መሆን ይጠበቅበታል (designed for liquid waste transport)
  • ተወዳዳሪው በስራዉ ላይ በቂ ልምድና ችሎታ ያለው መሆን ይጠበቅበታል
  • በቀን ውስጥ የሚያመርተውን የፍሳሽ ቆሻሻ ሙሉ በሙሉ ማንሳት።
  • ደህና ይዞታ ላይ ያለ የፍሳሽ ማንሻ መኪና ማቅረብ የሚችል።
  • በሚጭንበት፡ በሚያራግፍበትና በሚንቀሳቀስበት ቦታ ፍሳሽ ማንጠባጠብ የለበትም፡
  • ለስራው በቂ የሰው ሃይል መመደብ የሚችል
  • ከፍሳሽ አወጋገድ ጋር ያለውን ሃገራዊ ህጎች የተገነዘበ መሆን ይኖርበታል
  • የተሰጠውን ስራ በሃላፊነት የሚሰራ እና ድርጅቱን ከአሉታዊ ተፅዕኖ የሚጠብቅ (ከተፈቀደ ማራገፊያ ዉጭ አለመጠቀም፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ፈቃድ መጠየቅ)
  • የድርጅቱን የስራ ላይ ደህንነት እና የአካባቢ አያያዝ ህጎችን የሚከብርና የሚጠብቅ
  • ለሚያሰራቸው በቂ የስራ ላይ ደህንነት ቁሳቁሶችን ማቅረብ የሚችል (ጫማ፤ አንፀባራቂ፤ ግላብ፣ የስራ መነፅር)

ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የምትችሉና ፍላጎቱ ያላችሁ ተጫራቾች የተዘረዘሩትን ሰነዶች ወይም ማስረጃዎች እና የዋጋ ዝርዝር መስጫ በአንድ ጉዞ በመያዝ መካኒሳ በሚገኘው አዋሽ ወይን ጠጅ አ.ማ. ዋና መስሪያ ቤት ግዢ ክፍል በአካል በመምጣት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እንድታስገቡ እንጠይቃለን። ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0918913895 ወይም 0966334557 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

ማሳሰቢያ፡-

  • አዋሽ ወይን አ.ማ. ይሄን ማስታወቂያ በሙሉም ሆነ በከፊል የመቀየር ወይም የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • አዋሽ ወይን አ.ማ. የተሻለ መንገድ ካገኘ የንግድ መስፈርቶቹን የሚያሟላ ማንኛውንም አመልካች የመምረጥ መብቱ የተጠበቀ ነው።
Save Tender