አፈ/ከሳሽ… ፀደይ ባንክ ኢማ እራስ ጋይንት ቅርንጫፍ አፈ-ተከሳሽ ... 1. ታርቄ ምስጋናው አባተ 2. ወ/ሮ ሠናይት እርቅይሁን መካከል ስላለው የገንዘብ ክስ ክርክር ጉዳይ በጠኛ የአፈ/ተከሳሽ በታርቄ ምስጋናው ስም ተመዝግቦ የሚገኝ በነፋስ መውጫ ከተማ ቀበሌ 03 በአዋሳኝ ምስራቅ ቢራራ አበባው ምዕራብ መንገድ ስሜን አዲሱ ሲሳይ ደቡብ ደሳለኝ አስፋው ስፋቱ 162 ካ.ሜትር የሆነ ቤትና ቦታ በመነሻ ዋጋው 1,093,953.08 / አንድ ሚሊዮን ዘጠና ሶስት ሺ ዘጠኝ መቶ ሀምሳ ሶስት ብር ከስምንት ሳንቲም/ በሆነ በጨረታ ለመሸጥ የጨረታ ማስታወቂያ በእናንተ በኩል በማስነገር ውጤቱ እንዲቀርብ የጨረታ ማስታወቂያው አየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ 30 ቀናት ሲሆን ከጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ኅዳር 13 ቀን 2018 ዓ.ም ይሆናል፡፡
የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት በደ/ጎን/አስ/ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በደ/ታቦር ከተማ ቀበሌ 04 የሚገኘውን ቤት በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።