የሀበሻ ቢራ አክስዮን ማህበር የተለያዩ የምርት ግብዓቶችን እና የተለያዩ እቃዎችን ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የድርጅቱ ፋብሪካ ወደሚገኝበት ደብረ ብርሃን እና ከአዲስ አባባ ወደተለያዩ ከተሞች የደረቅ ጭነት የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ በዘርፉ የተሰማሩ የሀገር ውስጥ የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢ ድርጅቶችን በጨረታ በማወዳደር ከአሸናፊው ድርጅት/ቶች ውል በመፈራረም የአገልግሎት ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
የሀበሻ ቢራ አክስዮን ማህበር በዘርፉ የተሰማሩ ከደረጃ 1 እስከ 4 የሆኑ የሀገር ውስጥ የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢ ድርጅቶችን በጉዞ መስመር ከአሰላ ደብረብርሀን እና ከአዲስ አበባ ደብረ ብርሀን በጨረታ በማወዳደር ከአሸናፊው ድርጅት/ቶች ጋር እንደ ሁኔታው የሚታደስ ለ1 (አንድ) ዓመት ለምርት ግብአት የሚሆኑ ጥሬ እቃዎችን (ገብስ ‚ብቅል, ስኳር) የማጓጓዝ የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ ተፈሪርሞ መስራት ይፈልጋል።