የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፓሬሽን በአዋጅ ቁጥር 84/2016 በአንቀጽ 22 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ገንብቶ ከሚያስተላልፋቸው መደበኛ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በተጨማሪ በካፒታል ፕሮጀክት እየገነባ ለሽያጭ የሚያቀርባቸው የመኖሪያ ንግድ ቤቶች እንዳሉ ይታወቃል። በዚሁ መሰረት በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ግንባታቸው የተጠናቀቁና መሠረተ ልማት የተሟላላቸውን 545 ባለ አራትና ባለ አስራ አንድ ወለል ከፍታ ያላቸውን መኖሪያ ቤቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በሽያጭ ማስተላለፍ ይፈልጋል።