የደባርቅ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ፅ/ቤት በ 2019 በጀት ዓመት ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ በሎት አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
የደባርቅ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የደባርቅ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ፅ/ቤት በ 2019 በጀት ዓመት ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ በሎት አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
ስለዚህ:-
- ሎት 1- የመኪናና የማሽነሪ መለዋወጫ (ስፔርፓርት) እቃዎች
- ሎት 2 - የማሽነሪ እና የመኪናዎች ጎማና ባትሪ
- ሎት 3 - የደንብ ልብሶች
ስለዚህ ተጫራቾች ሊያሟሉት የሚገባቸው -
- ህጋዊ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው።
- ቲን ነበር ያላቸው
- የግዥ መጠን ብር 500,000 ( አምስት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
- የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለባችሁ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናቶች በመንግስት የስራ ሰዓት የጨረታ ሰነዱን በብር 100 /አንድ መቶ ብር/ መግዛት ይቻላል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ለሚጫረቱበት ጨረታ በየሎቱ በእያንዳንዱ ማለትም ለሎት 1- የማሽነሪና መኪና መለዋወጫዎች ስፔርፓርት ግዥ 20,000 ብር፣ ለሎት 2 ጎማና ባትሪ ግዥ 10,000 ብር፣ ሎት 3 የደንብ ልብሶች 10,000 ብር፣ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ፣ በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ በሞዴ 1 የተቆረጠ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ ተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ሆኖ መረጃውን ፖስታው ውስጥ አስገብተው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 13 በጋዜጣ ከታተመ ጊዜ ጀምሮ በ11 ኛ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ወይም ከዚያ በፊት አንድ ኦርጅናልና አንድ ፎቶ ኮፒ በታሸገ ፖስታ ከጨረታ ሳጥኑ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የመጫረቻ ሰነዱ ዋጋ ፀንቶ የሚቆየው ጊዜ 40 የስራ ቀናቶች ይሆናሉ።
- ጨረታው ቢሮ ቁጥር 13 በተገለጸው ቦታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመ ጊዜ ጀምሮ በ11ኛ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙ ከጠዋቱ በ4:30 ሰዓት ጨረታው ይከፈታል። በ11 ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የዕቃ ዓይነት ዝርዝር ከሚገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዕቃ ዝርዝር መረዳት ይችላሉ።
- አሸናፊው ድርጅት ንብረቱን ደባርቅ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 13 ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ሰነዱን በሚሞሉበት ሰዓት ስርዝ ድልዝ መኖር የሌለበት ሲሆን የእቃው ናሙና ቢሮ ቁጥር 13 በግንባር በመቅረብ ማየት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡ የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ሙሉ ስማቸውን ፊርማቸውን በሙሉ አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው።
- ጨረታው በሎት ጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ሙሉ በሙሉ በሞላ ስለሆነ ከመጫረቻ የዋጋ መሙያ ሰነዱ ላይ ክፍት ማድረግ የለባችሁም በተጨማሪም የዕቃዎች ብዛት ከበጀት አንፃር ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልጋቸው በስልክ ቁጥሮች 058 117 0033 ወይም 0581171208 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
ማሳሰቢያ:- ሁሉም ዕቃዎች ጥራቱን የጠበቀና በተጠየቀው ሞዴል መሰረት ኦርጅናል መሆን አለባቸው።
ተጨማሪ ማብራሪያዎች መረጃዎች ካሉ በቢሮአችን በውስጥ ሰሌዳ ማስታወቂያ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን።
የደባርቅ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Debark Town Urban and Infrastructure Development Office, Amhara, buys in three lots by open tender: vehicle and machinery spare parts, tyres and batteries, and uniforms. Bidders need a renewed trade licence, TIN, tax clearance and VAT for purchases over 500,000.
