Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወልቂጤ ዲስትሪክት
  • Address Oromia Ethiopia, Phone: ------
  • Website
  • Deadline10 Dec 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየሐራጅ ተሳታፊዎች የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/5ኛ ወይም 20% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ ሲ.ፒ.ኦ
  • opening dateታህሳስ 01 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 እስከ 6:00 በሸገር ከተማ ገላን ክ/ከተማ በሚገኘው የባንኩ መጋዘን ውስጥ
  • Categories Industrial Machinery Provision And Installation , Sales, Disposals And Foreclosure , Business, Industry And Factory Foreclosure

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወልቂጤ ዲስትሪክት ያልተከፈለ የሊዝ ክፍያ ምክንያት የተረከባቸውን የካፒታል ዕቃዎች በሁለተኛ ዙር ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወልቂጤ ዲስትሪክት


የሁለተኛ ዙር የሐራጅ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወልቂጤ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት የባንኩ ደንበኛ የወሰደውን የካፒታል ዕቃ ኪራይ ክፍያ በገባው የሊዝ ውል መሰረት ኪራይ ለመክፈል ባለመቻሉ በባንኩ ስም ተመዝግበው ደንበኛው ተከራይቶ የነበረውን እና ባንኩ ከተከራዩ የተረከበውን የካፒታል ዕቃዎች በሊዝ አዋጅ ቁጥር 103/1990 እና በተሻሻለው የካፒታል ዕቃ ኪራይ አዋጅ ቁጥር 807/2005 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ንብረቶቹን ባሉበት ሁኔታ በሁለተኛ ዙር በሐራጅ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ተ.ቁየተከራዩ ስምየሚሸጠው ንብረት አይነት እና ዝርዝር መረጃንብረቱ የሚገኝበት አድራሻየሐራጅ መነሻ ዋጋ (በብር)የንብረቱ ሁኔታሐራጁ የሚካሄድበት ቦታሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓትየሐራጅ ደረጃ
1ትዝታ፣ተሻለና ቤተሰቦቹ ዳቦና ኬክ አምራች ህብ/ሽ/ ማህበር
  1. Rotary Over 16 Tray የዳቦ ማከፈሻ አንድ (01) Set
  2. Volumetric Dough Divider የሊጥ ማከፋፈያ (01) set.
  3. Mixer የሊጥ መቀላቀያ (01) set
  4. Proofer For Rotary oven with Steam Generator (01) Set
  5. Molding Machine የሊጥ ቅርጽ ማውጫ (01) Set
  6. Bread Slicer የዳቦ መቁረጫ አንድ (1) Set
  7. French Bread Tray and Rottey for ATDF250 ሁለት (02) Set
  8. Flat Tray with Trolley for ATDF 250 ሁለት (02)
  9. Diesel Generator አንድ (01) Set ናቸው።
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ሸገር ከተማ ገላን ክ/ከተማ በሚገኘው የባንኩ መጋዘን ውስጥ9,373,294.86አዲስበኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ሸገር ከተማ ገላን ክ/ከተማ በሚገኘው የባንኩ መጋዘን ውስጥታህሳስ 01 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 እስከ 6:002ተኛ

የሐራጅ መመሪያ (በከፊል)

  • የሐራጅ ተሳታፊዎች የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/5ኛ ወይም 20% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ ሲ.ፒ.ኦ በማቅረብ በሐራጁ ላይ መሳተፍ ይችላል።
  • በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም አካል ከቀረጥ ነፃ የመጠቀም ተመሳሳይ መብት ያለው ከሆነ ወይም መንግስት በንብረቶቹ ላይ የሚያስከፍለውን የቀረጥ ክፍያ ለመክፈል ፈቃደኛ የሆነ ሁሉ በሐራጅ ጨረታው መሳተፍ ይችላል።
  • የሐራጁ አሸናፊ ንብረቶቹን ሙሉ ለሙሉ በካሽ/በጥሬ ገንዘብ ለመግዛት ተወዳድሮ ካሸነፈ ንብረቱን የሸጠበት ዋጋ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን እና ሌሎች ግብር እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰኑ የታክስ ክፍያዎችን ጨምሮ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል።
  • የሐራጅ አሸናፊ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን (VAT) ፣ ንብረቶቹን በጥሬ ገንዘብ ወይም በእጅ በእጅ ሽያጭ የሚገዛ ከሆነ ከቀረጥ ነፃ መብት የመጠቀም ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል።
  • በሐራጅ ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
  • ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ታህሳስ 01 ቀን 2019ዓ.ም ከጠዋቱ 4 ሰአት እስከ 6 ሰአት ይካሄዳል።
  • ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሐራጁን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ሐራጁን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-365-91-44/011-365-89-43 ደውሎ ማግኘት ይቻላል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወልቂጤ ዲስትሪክት

✨ messages.ai_summary
Development Bank of Ethiopia, Welkite District, sells by second-round auction repossessed lease-financed bakery equipment (rotary oven, dough divider, mixer, proofer, moulder, bread slicer, trays and a diesel generator) at its warehouse in Gelan Sub-City, Sheger City, as is.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender