ኤም.ዲ.ኤን.ኤን የትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶች እና በአዳማ የሚገኝ መጋዘን ሽያጭ
የኤም.ዲ.ኤን.ኤን ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር
የጨረታ ማስታወቂያ
1ኛ. ኤም.ዲ.ኤን.ኤን የትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር የሠሌዳ ቁጥራቸው ኢት 03-68851 እና ኢት 03-68852 የሆኑትን የእያንዳንዳቸው የጭነት መጠናቸው 63 ሰው የአካሉ አይነት ከፍተኛ የሕዝብ የተፈቀደለት የስራ ፀባይ ለንግድ አገልግሎት የሆኑትን ተሽከርካሪዎች የጨረታ መነሻ ዋጋ ለሰሌዳ ቁጥር ኢት 03-68851 ብር 8.3 ሚሊዮን እና ለሰሌዳ ቁጥር ኢት 03-68852 ብር 8 ሚሊዮን
2ኛ. በአዳማ ከተማ በሬቻ ወረዳ የቤት ቁጥር 216 የሚገኘውን በይዞታ ሰርተፍኬት የተረጋገጠ 1021.98 ካ/ሜ ቦታ እና በቦታው ላይ የተሰራ መጋዘን
የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 26,366,149.65 በጨረታ ለመሸጥ አስቧል::
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን መነሻ ዋጋ 25% (ሃያ አምስት በመቶ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ(ሲ.ፒ.ኦ) አሰርተው ጨረታው በሚካሄድበት እለት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ አዳማ ፓንአፍሪክ ሆቴል ገባ ብሎ ሰላም ሆቴል ፊት ለፊት ምስራቅ ደቡብ የህዝብ ማመላለሻ ማህበር ጽ/ቤት በሚገኘው በአክሲዮኑ ቢሮ ቁጥር 10 በተዘጋጀ ሳጥን ታህሳስ 7 ቀን 2019 ጠዋት 3:30 ማስገባት አለባቸው::
- ጨረታው ታህሳስ 7 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 4:00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል::
- ከላይ የተዘረዘሩት ንብረቶች ጨረታ ከላይ በተገለፀው ቀንና ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበት የኩባንያው ዋናው መ/ቤት በሚገኝበት ህንጻ ውስጥ ይካሄዳል::
- ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል:: ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበ ተጫራች ግን ኩባንያው ዋጋውን የሚቀበል መሆኑን አለመሆኑን ጨረታው ከተደረገበት ቀን ቀጥሎ ባሉት አምስት የስራ ቀናት ውስጥ ለተጫራቾች ያሳውቃል::
- የጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራች የአሸናፊነት ደብዳቤ ከኩባንያው ከተቀበለበት ቀን ጀምሮ የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀናት ውስጥ ለኩባንያው ገቢ በማድረግ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል::
- ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገቢ ለማያደርግ ተጫራች ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለኩባንያው ገቢ ይደረጋል::
- ሁሉንም ንብረቶች በማስተላለፍ ሂደት ለመንግስት የሚከፈል ማንኛውንም ክፍያ ገዢ ይከፍላል::
- ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 0911253136 ወይም 0943254646 ወይም 0911659730 ወይም 0902292710 መደወል ወይም በአካል ቀርቦ ማነጋገር ይቻላል::
ኩባንያው ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ኤም.ዲ.ኤን.ኤን የትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር
✨ messages.ai_summary
MDNN Transport Share Company is selling two 63-seat public transport buses and a 1,021.98 square metre plot with a warehouse in Bireche Woreda, Adama. Bids are opened at its Adama office. Open bid.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
