የደሴ አካል ተሀድሶ ማእከል ለ2019 በጀት አመት ለማእከሉ አገልግሎት የሚውሉ የጽህፈት መሳሪያዎች የጽዳት እቃዎች ፣ የህንጻ መሳሪያዎች፣ የደንብ ልብስ ፣ የደንብ ጫማ፣ የህክምና እቃዎች፣ የህትመት ስራዎች የመኪና ዘይት እና ቅባት፣ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች የፎቶ ኮፒና የኮምፒውተር ጥገና አገልግሎት አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፤
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በደቡብ ወሎ መስ/ዞን ደሴ አካል ተሀድሶ ማዕከል
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የደሴ አካል ተሀድሶ ማእከል ለ2019 በጀት አመት ለማእከሉ አገልግሎት የሚውሉ የጽህፈት መሳሪያዎች የጽዳት እቃዎች ፣ የህንጻ መሳሪያዎች፣ የደንብ ልብስ ፣ የደንብ ጫማ፣ የህክምና እቃዎች፣ የህትመት ስራዎች የመኪና ዘይት እና ቅባት፣ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች የፎቶ ኮፒና የኮምፒውተር ጥገና አገልግሎት አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፤
ስለሆነም:-
- የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣ የግብር መክፈያ ቁጥር /TIN/ ያለው የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ ፤ ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን የሚያሟላ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች የጨረታ መመሪያውንና የእያንዳንዱን እቃዎች ዝርዝር መግለጫ / Specification / የያዘ የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00/ ሶስት መቶ ብር / በመክፈል ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 7 መግዛት ይቻላል!!
- የጨረታ ማስከበሪያ በሞሉት ጠቅላላ ዋጋ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ /1%/ አንድ ፐርሰንት /ማቅረብ አለባችሁ።
- የጨረታ ውድድሩ የሚደረገው በሎት ሆኖ በጠቅላላ ዋጋው ነው።
- ጨረታውን በሚወዳደሩበት ጊዜ የተጋነነ ዋጋዎችን በገበያ ጥናት መሰረት በማድረግ ከውድድር ውጭ የምናደርግ መሆኑን እንገልፃለን።
- የጨረታ ሰነዱ በታሸገ ፖስታ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ከ10ኛው ቀን ቀጥሎ በዋለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3:30 ድረስ በመቅረብ ቢሮ ቁጥር 7 በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ሳጥን ማስገባት ይጠበቅል
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ተከታታይ የስራ ቀን ቀጥሎ በሚውለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3:30 ታሽጎ በእለቱ ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማእከሉ ቢሮ ቁጥር 7 ጨረታው ይከፈታል።
- ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሁሉም ተጫራቾች በአካል ባይገኙም በእለቱ የጨረታ ሰነዱ ተከፍቶ ከታየ በኋላ ተገቢው የጨረታ ማስከበሪያ መኖሩ ከተረጋገጠ ተጫራቹ በአካል ባይገኝም ጨረታው ይከፈታል።
- የጨረታ አሸናፊው በተሰጠው የጨረታ ሰነድ /Specification/መሰረት ለማቅረብ ውለታ በወሰደበት ቀናት ውስጥ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ በማቅረብ በሚመለከታቸው ቴክኒክ ባለሙያ እየተረጋገጠ ለማእከሉ ን/ክፍል በሞ/19 ገቢ ማድረግ ይጠበቅበታል ።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 7 በአካል በመገኘት ወይም በቢሮ ስልክ ቁጥር 0333116263 - 0333124956 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የደሴ አካል ተሀድሶ ማእከል
✨ messages.ai_summary
Dessie Physical Rehabilitation Center buys by open tender: stationery, cleaning items, building materials, uniforms and shoes, medical items, printing, vehicle oil and lubricants, spare parts, and photocopier and computer repair. Bidders need a renewed licence, TIN and VAT.
