Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Agricultural Businesses Corporation (የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን)
  • Address ሳሪስ አቦ ፋፋ የምግብ አክሲዮን ጎን 200 ሜትር ገባ ብሎ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114709095
  • Websitehttps://ethioagri.com/
  • Deadline24 Nov 2026, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document Priceብር 500.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityከጠቅላላ ዋጋ ከ2% ያላነሰ (CPO)
  • opening dateህዳር 15 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት፣ በዘርፉ ጽ/ቤት
  • Categories Agriculture And Farming , Food Items And Drinks

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ የነጭ የዳቦ ስንዴ የምግብ እህል ግዥ

Ethiopian Agricultural Businesses Corporation (የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን)


የጨረታ ማስታወቂያ

በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ

ስንዴ የምግብ እህል ግዥ ጨረታ

የጨረታ ቁጥር ኢግስኮ-የም/ዘ/አ/ዘ/ምዘ/ሸ01/2019

በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን-አዲስ አበባ ነጭ የዳቦ ስንዴ የምግብ እህል የሃገር ውስጥ ምርት ከአቅራቢዎች ከነመቋጠሪያው በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል:: ስለሆነም ነጭ የዳቦ ስንዴ የምግብ እህል በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ መስፈቱን የሚያሟሉ ሁሉ በጨረታው መሳተፍ ይችላል::

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክርነት ወረቀት፤ የንግድ ምዝገባ የምስክርነት ወረቀት፤ በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የምስክርነት ወረቀት(ክሊራንስ) እና በመንግስት ግዥ መመሪያ መሰረት በመንግስት ግዥ አቅርቦት የተመዘገበ መሆን ኮፒ ማቅረብ የሚችል አለበት::
  2. ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ከ2% ያላነሰ በባንክ የተመሰከረ CPO በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፓሬሽ የግብርና ውጤቶች ሽያጭና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ዘርፍ ስም ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነዶች ጋር በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል:: የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ለ30 ቀናት የፀና መሆን ይኖርበታል::
  3. ማንኛውም ተጫራች የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የሚጠይቀውን በሙሉ አሟልቶ ማቅረብ ይጠበቅበታል:: የዶሮ ተረፈ ምርት(የዶሮ ኩስ) ሽያጭ ተጫራቹ በሚሰጠው ዋጋ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ይጨመራል::
  4. ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (ብር አምስት መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መከፈቻ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ሀሙስ፣ ከሰዓት በፊት ከ2:00-6:00፣ከሰዓት በኋላ ከ7:00-10:30 እንዲሁም ዓርብ፣ ከሰዓት በፊት ከ2:00- 5:30፣ከሰዓት በኋላ ከ7:30-10:30 በግብርና ግብዓት ግቢ 2ኛ ፎቅ በመገኘት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ::
  5. ተጫራቾች በኤንቬሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣብ ቀን ጀምሮ እስከ ህዳር 15 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ በ8:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለበት፤ ጨረታው ህዳር 15/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ህዳር 15 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ በ8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዘርፉ ጽ/ቤት ጨረታው ይከፈታል::
  6. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም::
  7. ዘርፉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለተጨማሪ መረጃ
ስልክ ቁጥር:- 09-41-00-68-72/09-81-73-70-12
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን

✨ messages.ai_summary
Ethiopian Agricultural Businesses Corporation (Improved Seed Supply Sector) seeks licensed suppliers of locally produced white bread wheat for food, including packaging. Open bid.
Save Tender