Tender Detail

Tender Details

  • Company በጋሞ ዞን የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት
  • Address በጋሞ ዞን አርባምንጭ ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-181-40-91
  • Website
  • Deadline22 Nov 2026, 11:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 200 (የማይመለስ)
  • Bid Securityሎት 1-3 እና 5 ብር 30,000፤ ሎት 4 ብር 10,000 (በጥሬ ገንዘብ ወይም CPO)
  • opening dateበዕለቱ 8:00 ሰዓት
  • Categories Electrical And Electromechanical , Printing And Publishing , Food Items And Drinks , Furniture , Cloth And Shoes

የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት የደንብ ልብስ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ ሕትመት እና የታሸገ ውሃ ግዥ

በጋሞ ዞን የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

በጋሞ ዞን የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት የተለያዩ የግዥዎች ማለትም :-

  • ሎት-1 የሠራተኞች ደንብ ልብስ ለመጀመሪያ ግዜ የወጣ
  • ሎት-2 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ ለመጀመሪያ ግዜ የወጣ
  • ሎት-3 የፈርኒቸር ዕቃዎች ግዥ ለመጀመሪያ ግዜ የወጣ
  • ሎት-4 የተለያዩ የሕትመት አገልግሎት ግዥ ለመጀመሪያ ግዜ የወጣ
  • ሎት-5 የተለያዩ የታሸጌ ውሃ ግዥ ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ

በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::በዚሁ መሠረት በጨረታው መሳተፍ የሚትፈልጉ በዘርፉ የተሰማራችሁ ድርጅቶችና ግለሰቦች ለጨረታው ውድድር ማቅረብ ያለባችሁ መስፈርቶች የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ፤ የንግድ ስራ ምዝገባ ሰርትፍከት፤የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፍከት፤የግብር መከፈያ ቁጥር የአቅራቢነት ሰርትፍኬትና የጨረታ ማስከበሪያ ከሎት1--ሎት 3እና ሎት-5 ላሉት ብር 30,000 /ሰላሳ ሺህ /ብር ሎት-4 10,000/አስር ሺህ/ ብር በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ ክፍያ ማዘዣ CPO ከታወቁ ባንክ በማዘጋጀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው:: ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከመ/ቤቱ ግዥና ንብረት አስተዳዳር ዘወትር በስራ ሰዓት በመቅረብ የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ/ ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ::በሁሉም አሸናፊ የሚሆኑ ተጫራቾች ከመ/ቤቱ ጋር ውል በመግባት ጥራት ያላቸውን ኦርጅናል ዕቃዎች ብቻ አቅርቦ ለማስረከብ ፈቃደኛ የሆኑ መሆን አለባቸው::ያቀረቡት ዕቃ በባለሙያ ተገምግሞ የጥራት ጉድለት ስታይ ወዲያውኑ የመቀየር ኃላፊነት ግዴታ የሚቀበል መሆን አለበት:: ተጫራቾች የጨረታ ዋጋው ያለስርዝና ድልዝ በጥንቃቄ በመሙላት በሰነዱ ላይ ፍርማና ማህተም፣ የጨረታውን ዓይነት እና ስልክ በመጻፍ በዕለቱ ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው:: ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 ተከታታይ ስራ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 5:00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ በዕለቶ 8:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል:: 16ኛው ቀን ድንገት የሥራ ቀን ሳይሆን ስቀር በሚቀጥለው ስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ሂደቱ ይከናወናል:: መ/ቤቱ የተሸሌ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፍል ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው::

አድራሻ፤- ከመዲኃኒዓለም ቤቴክርስቲያን ዝቅ ብሎ ወደ የትነበሪሽ ማዞሪያ ላይ ባለው ዲንጉዛ ሕንፃ ውስጥ እንገኛለን::

አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Arba Minch Zuria Woreda Finance and Plan Development Office (Gamo Zone) seeks suppliers in 5 lots: staff uniforms, electronics, furniture, printing services and bottled water. Open bid.
Save Tender