Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት
  • Address ማዘጋጃ ቤት 2ኛ ፎቅ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ክፍለ ከተማ አራዳ ወረዳ 1 ሚኒሊክ አደባባይ /ፒያሳ/ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0118680464
  • Website
  • Deadline19 Nov 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200(ሁለት መቶ ብር)
  • Bid Securityሎት 1 የጥናት አገልግሎት 100,000፤ ሎት2 የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት 1000፤ ሎት3 የጉልበት ስራ 1000 — በባንክ የተረጋገጠ CPO
  • opening date8:30 ይከፈታል፣ ነገር ግን 11ኛ ቀን የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለው የሥራ ቀናት ውስጥ የሚከፈት ይሆናል።
  • Categories Consultancy Service , Textile, Garment & Leather , Study And Research And Tools , NonConsultancyServices

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የግዥና ን/አስ/ጠቅ/አገ/ዳይሬክቶሬት በ2019 በጀትዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትይፈልጋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት


ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ/

የጨረታ ቁጥር 002/2019በድጋሚ የወጣ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የግዥና ን/አስ/ጠቅ/አገ/ዳይሬክቶሬት በ2019 በጀትዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትይፈልጋል።

ተ.ቁሎቶችየዕቃው ዓይነትየሚያስዙት የጨረታ ማስከበሪያ/CPO
1ሎት 1የጥናት አገልግሎት100,000
2ሎት2የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት1000
3ሎት3የጉልበት ስራ የዓመት ውል በመያዝ የተለያዩ ስራዎችን ለማሰራት1000

መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው -

  1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው መሆኑን፣
  2. የዘመኑን ግብር የከፈለ መሆኑን አለበት፣
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማቅረብ የሚችል፣
  4. የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ያለው፣
  5. የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር Tin No ያለው፣
  6. ተጫራቾች በባንክ የተረጋገጠ በጽ/ቤታችን ስም CPO ማስያዝ አለባቸው ነገር ግን CPO ያላስያዙ ቢኖር ከጨረታ ውጪ ይሆናል
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት የሚችሉት ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ይሆናል
  8. ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ለመወዳደር ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለሚወዳደሩብት ዕቃዎች ናሙና መቅረብ አለበት፣
  9. ማንኛውም ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1 እስከ 5 የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ፒያሳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው ማዘጋጃ ቤት የከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፣
  10. አሸናፊው ድርጅት ጥራቱን ያልጠበቀ ዕቃ ወይም አገልግሎት ካቀረበ በራሱ ወጪ የመለወጥ ግዴታ አለበት፣
  11. መ/ቤቱ ካቀረበው ሰነድ ውጪ በሌላ ሰነድ በአማራጭነት ማቅረብ አይቻልም፣ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ቴክኒካል ኦርጅናል እና ፋይናንሻል ኦርጂናል ዋጋ ሞልታችሁ በተናጠል (ለየብቻ እንዲሁም ቴክኒካል ኮፒ እና ፋይናንሻል ኮፒ በፖስታ አድርጋችሁ የድርጅታችሁን ማህተምና ፊርማ በማድረግ በግዥና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 342 ለጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባችሁ፣
  12. ጥቃቅን አነስተኛ ተጫራቾች ለምትጫረቱባቸው ዕቃዎች የጨረታ ሰነዱን በነፃ ለመውሰድ
    ሀ. ካደራጃችሁ መ/ቤት ደብዳቤ ማምጣት አለባችሁ
    ለ ሰነዱን በነፃ ለመውሰድ በመመሪያ መሰረት ለምታቀርቡት ዕቃ አምራች መሆን አለባችሁ፣
  13. ተጫራቾች ጽ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት በትክክል መሙላት አለባቸው።
  14. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ አሸናፊው ድርጅት ባሸነፈበት ዕቃ ወይም አገልግሎት ላይ ውል ሲገባ የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል እንዲሁም አሸናፊ የሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት ጨረታ ተከፍቶ ውጤት ከተለጠፈ ከ8 የሥራ ቀናት በኋላ በመቤታችን ቀርቦ ውል መግባት አለበት
  15. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ጋዜጣው ከወጣበት ከ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ11ኛ ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ታሽጎ 8:30 ይከፈታል፣ ነገር ግን 11ኛ ቀን የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለው የሥራ ቀናት ውስጥ የሚከፈት ይሆናል።

ማሳሰቢያ:-1. ተጫራቾች የቀረበው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆኑንና ያላካተተ መሆኑን መግለፅ አለባችሁ ይህ ካልሆነ ግን መ/ቤቱ የቀረበውን ዋጋ ቫትን እንዳካተተ አድርጎ ይወስደዋል።

28. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ:-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ማዘጋጃ ቤት ከንቲባ ግቢ ውስጥ/ ክፍለ ከተማ አራዳ ወረዳ1 ፒያሳ ምኒሊክ አደባባይ /ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን/ ፊት ለፊት ምኒልክ አደባባይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር:- 0970636847 ወይም 0938535903 ይደውሉ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Addis Ababa City Administration City Manager’s Office re-advertises a national open tender in three lots: a study service, uniform sewing, and an annual labour contract for various jobs. Bidders need a renewed licence, trade registration, paid tax, VAT, TIN and supplier certificate.
Save Tender