በየካ ክ/ከ የወ01 ጤና ጣቢያ በ2019 በጀት አመት በመንግስት ከተመደበለት ትሬዠሪና የውስጥ ገቢ መደበኛ በጀት በ1ኛ ዙር ብሄራዊ ግልፅ ጨረታ የተለያዩ መድኃኒቶችን የህክምና መሳሪያዎችን እና የላብራቶሪ ሬኤጀንቶችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በየካ ክ/ከ የወ 01 ጤና ጣቢያ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨ.ቁ.001/19
በየካ ክ/ከ የወ01 ጤና ጣቢያ በ2019 በጀት አመት በመንግስት ከተመደበለት ትሬዠሪና የውስጥ ገቢ መደበኛ በጀት በ1ኛ ዙር ብሄራዊ ግልፅ ጨረታ የተለያዩ መድኃኒቶችን የህክምና መሳሪያዎችን እና የላብራቶሪ ሬኤጀንቶችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች
- የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- በመድኃኒት ግዥ አቅራቢነት የተፈቀደበት ከምግብና መድሀኒት ቁጥጥር ኤጀንሲ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር /ብቻ በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው የስራ ቀን 11:30 ሰዓት ድረስ ከተቋሙ ግዥ ክፍል መውሰድ የምትችሉ ሲሆን የጨረታ ሰነዱ ላይ የሚጫረቱበትን ዋጋ በመሙላት እና ስም ፤ፊርማና የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም በማድረግ ዋናውንና ኮፒ በታሸገ ኢንቨሎፕ በተቋሙ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲ.ፒ.ኦ/ ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር /ብቻ በማሰራት ዋናውን/ኦርጅናል ከሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው የሚከፈተው ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 3:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በይፋ ይከፈታል።
- የውል ማስከበሪያ የምታሸንፉበትን አጠቃላይ የብር መጠን 10% ሲፒኦ ውል ስትገቡ ማስያዝ አለባችሁ።
- መድኃኒቶቹ እንዲሁም ሬአጀንቶቹ በተሰጠው ስፔስፊኬሽን መሰረት መቅረብ አለባቸው ኤክስፓየርድ ዴት ለሚያስፈልጋቸው መድሀኒትም ሆነ ሬአጀንቶቹ የተመረቱባቸውና ኤክስፓየርድ ጊዜያቸው በግልጽ የሚታይ መሆን አለባቸው። የአገልግሎት ጊዜያቸው ቢያንስ አንድ አመት እና ከዚያ በላይ መሆን አለባቸው።
- ዋጋ ስትሞሉ አጠቃላይ የሞላችሁትን ዋጋ ድምር ማስቀመጥ ይጠበቅባችኋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አሸናፊ ተጫራች ውል ከወሰደበት ጊዜ ጀምሮ በ5 ቀን ውስጥ መድኃኒቶችና ላብራቶሪ ሬኤጀንቶች እና የህክምና መሳሪያዎች ገቢ ማድረግ አለበት። ነገር ግን በድርጅቱ መጓተት ምክንያት መ/ቤቱ ስራውን ለመስራት ቢቸገር እርምጃ ለመውሰድ የምንገደድ መሆኑን እንገልጻለን።
- ጨረታ ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ ለ60 (ለስልሳ ቀን)
አድራሻ:- ፈረንሳይ ወደ አርባ አንድ እየሱስ በሚያስገባው መንገድ ገባ ብሎ ከወረዳ 01 አስተዳደር ጽ/ቤት አጠገብ። ለበለጠ መረጃ:- ስ.ቁ 0111-548454/0111-549680
በየካ ክ/ከተማ የወ01 ጤና ጣቢያ
✨ messages.ai_summary
Yeka Sub-City Woreda 01 Health Center, Addis Ababa, buys medicines, medical equipment and laboratory reagents through a national open tender (first round). Bidders need a renewed trade licence, TIN, VAT and a medicine supply licence from the Food and Drug Authority.
