የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ካስገነባቸው ዘመናዊ ህንፃዎች ውስጥ ለመኖሪያ ገስት ሃውስ አገልግሎት የሚውሉ ቤቶችን በውጪ ምንዛሬ ተመን በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ ብ.ግ. ጨ/አገ/17/02/2019 ተጫራቾችን አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል::
Federal Housing Corporation (የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን)
የ9ኛ ዙር የመኖሪያ/ገስት ሀውስ ቤቶች የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብ.ግ .ጨ/አገ/17/02/2019
- የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ካስገነባቸው ዘመናዊ ህንፃዎች ውስጥ ለመኖሪያ ገስት ሃውስ አገልግሎት የሚውሉ ቤቶችን በውጪ ምንዛሬ ተመን በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ ብ.ግ. ጨ/አገ/17/02/2019 ተጫራቾችን አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል::
- ኮርፖሬሽኑ ለሚያከናውነው የመኖሪያ ገስት ሃውስ ቤቶች ኪራይ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን እና የመወዳደሪያ ተመን ዋጋ በአንድ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው::
- ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ ሥርዓትና ይኸንኑ አስመልክቶ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን መመሪያ መሰረት ነው::
- ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች የተሟላ የጨረታ ሰነዱን ከጥቅምት 27 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ህዳር 11 ቀን 2019 ዓ.ም ቅዳሜን ጨምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ 2:00 እስከ 11:00 ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 6:00 ድረስ የማይመለስ ብር 1,000.00 አንድ ሺህ ብር/ በካሽ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድን በኮርፖሬሽኑ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት በሚገኘው ዋና የመሰብሰቢያ አዳራሽ 1ኛ ፎቅ ለዚሁ ታስቦ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በመጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ወይም ህዳር 11 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት 11:00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 / ሀምሳ ሺህ ብር/ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ሲ.ፒ.ኦ በፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው:: ከጨረታው መክፈቻ ዕለትና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፣ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጨረታ ሰነዱ ክፍል 1 ላይ በተገለፀበት ቀንና ሰዓት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ቤቶቹን በአካል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ማብቂያው ቀን ድረስ በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3:00 እስከ ቀኑ 11:00 ሰዓት ቤቶቹ በሚገኙበት አድራሻ ድረስ በመቅረብና ለዚሁ ስራ በሚመደቡ ባለሙያዎች እና በሚወጣው ፕሮግራም መሰረት ቤቶቹን መመልከት ይችላሉ።
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ መረጃ
በስልክ ቁጥር 0910-48-59-48 ወይም 0922-98-76-33 ወይም 0922-49-18 85 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል::
ዌብሳይት/ website www.fhc.gov.et
P.O. Box 299
ፋክስ ቁጥር: 011-5-54-60-45/ 011-5-52-46 46
የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን
✨ messages.ai_summary
Federal Housing Corporation offers, in its 9th round, residential guest-house units in its modern buildings for rent, priced in foreign currency, through national open bidding. Interested bidders may view the units before bidding.
