Tender Detail

Tender Details

  • Company Ministry of Foreign Affairs
  • Address , Phone: 00 00 00 00
  • Website
  • Deadline16 Nov 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityተወዳዳሪዎች የታዘዘውን የጨረታ ማስከበሪያ CPO ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማያያዝ አለባቸው።
  • opening dateበዕለቱ በ8:30 ላይ ይከፈታል።
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በካዛንቺስ ባስገነባው አዲስ አፓርትመንት ሕንፃ በሙሉ (ሙሉ ሕንፃውን) መከራየት ለሚፈልጉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ፣ ኩባንያዎች ወይም ፍላጎት ላላቸው አካላት በኪራይ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።

Ministry of Foreign Affairs


ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ የአፓርትመንት ሕንፃ ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በካዛንቺስ ባስገነባው አዲስ አፓርትመንት ሕንፃ በሙሉ (ሙሉ ሕንፃውን) መከራየት ለሚፈልጉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ፣ ኩባንያዎች ወይም ፍላጎት ላላቸው አካላት በኪራይ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።

የሕንፃው ዝርዝር መግለጫ

አድራሻ: ካዛንቺስ፣ አዲስ አበባ

የወለል መጠን: ምድር ስር 2 ወለል (B+2) + ሜዛኒን + ምድር + 18 ወለል (G+18)

የመኖሪያ አፓርትመንቶች (በአጠቃላይ 150 ክፍሎች):

  • ባለ 3 መኝታ አፓርትመንት: 24 ክፍሎች
  • ባለ 2 መኝታ አፓርትመንት: 42 ክፍሎች
  • ባለ 1 መኝታ አፓርትመንት: 48 ክፍሎች
  • ስቱዲዮ (Studio) አፓርትመንት: 36 ክፍሎች

ተጨማሪ አገልግሎቶች:

  • የራሱ ግቢ ያለው (Own Compound)
  • ጀነሬተር (Standby Generator)
  • መኪና ማቆሚያ የሚሆኑ 2 ምድር ወለሎች (B+2 Underground Parking)
  • በግራውንድ እና ሜዛኒን ወለሎች ላይ ለቢሮ፣ ለንግድ፣ ለባንክ ወይም ለሌሎች አገልግሎቶች የሚውሉ ሰፊ ቦታዎች

የመወዳደሪያ መስፈርቶች

  • ተወዳዳሪዎች ሕጋዊ የድርጅት ምዝገባ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የውክልና ሰነድ ማቅረብ አለባቸው።
  • ፍላጎት ያላቸው ተቋማት ሙሉ ህንፃውን ለመከራየት የሚያስችላቸውን የፋይናንስና የቴክኒክ ፕሮፖዛል በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ተወዳዳሪዎች የታዘዘውን የጨረታ ማስከበሪያ CPO ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማያያዝ አለባቸው።

መረጃና የቦታ ጉብኝት:- ፍላጎት ያላቸው አካላት የህንፃውን ዝርዝር ፕላን ለመመልከት፣ የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ እና ሕንፃውን በአካል ተገኝተው ለመጎብኘት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር (10) ተከታታይ ሥራ ቀናት በሥራ ሰዓት ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ ማግኘት ይችላሉ። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር (10) ተከታታይ ሥራ ቀናት በ10ኛው ቀን ከሰዓት 8:00 ታሽጎ በዕለቱ በ8:30 ላይ ይከፈታል።

አድራሻ:- ሒልተን ሆቴል ፊት ለፊት አዲሱ ሕንፃ 3ኛ ወለል፣ ስልክ ቁጥር +251115531782/+251930470796/+251978738565

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

✨ messages.ai_summary
Ministry of Foreign Affairs re-advertises the lease of its whole new B+2+G+18 apartment building in Kazanchis, Addis Ababa: 150 units plus office and commercial floors, generator and underground parking. Open to international organizations, diplomats and companies with registration and TIN.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender