ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት የመንግሥት የልማት ድርጅት ሲሆን ከ 2017 በጀት ዓመት ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ የበጀት ዓመታት (እ.ኢ.አ የ2017፣ የ2018 እና የ2019) የሂሳብ መርማሪ (ኦዲተር) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመግባት ለማሠራት ይፈልጋል።
Emergency Relief Transport Enterprise (ERTE) (የዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት)
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የውጭ ኦዲት አገልግሎት ግዥ
በግዥ መለያ ቁጥር: ERTE/NCB/Serv/003/2019
ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት የመንግሥት የልማት ድርጅት ሲሆን ከ 2017 በጀት ዓመት ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ የበጀት ዓመታት (እ.ኢ.አ የ2017፣ የ2018 እና የ2019) የሂሳብ መርማሪ (ኦዲተር) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመግባት ለማሠራት ይፈልጋል።
በዚህም መሠረት በግልፅ ጨረታው ላይ የሚሳተፉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መረጃዎች ማሟላትና ማቅረብ አለባቸው።
- ከሚመለከተው አካል በዘርፉ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የወሰደና የታደሰ፤
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ የምዝገባ ሠርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሠርተፍኬት፣ ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ተቀባይነት ያለው የግብር ክሊራንስ (ታክስ ክሊራንስ) በአቅራቢነት (EGP) ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ፤
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ (CPO) ወይም ሕጋዊ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ የሚችል።
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል አቃቂ ቃሊቲ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት የፋይናንስ ዲፓርትመንት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የሥራ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በዚያኑ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4:30 ይከፈታል፤ ነገር ግን የጨረታ መክፈቻው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተገለፀው ቦታና ሁኔታ ይሆናል፤
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የድርጅቱ የሥራ ሰዓት
- ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ጠዋት ከ2:00 ሰዓት - 6:00 ሰዓት
- ከሰዓት ከ7:00 ሰዓት - 11:00 ሰዓት ፤ ቅዳሜ እስከ 10:00 ሰዓት
አድራሻ:- አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከሸገር ዳቦ ፋብሪካ ፊት ለፊት አሁን ትራን ባትሪ መሸጫ ሕንፃ በስተጀርባ 70 ሜትር ገባ ብሎ
ስልክ ቁጥር 0114390075/1569/3592/0114391027
ፋክስ 0114-39-63-36 ፖ.ሳ.ቁ. 2562
አዲስ አበባ
ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት
✨ messages.ai_summary
Emergency Relief Transport Enterprise seeks a licensed external auditor for three consecutive financial years. Bidders need a renewed professional competency certificate, trade licence, registration, TIN, VAT, tax clearance and EGP supplier registration.
