የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 09 ቀስተ ደመና ት/ቤት የቢሮና የትምህርት፣ የጽዳት፣ የደንብ ልብስ፣ የጥገና ዕቃዎችና የህትመት ግዥ
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 የቀስተ ደመና አፀደ ህፃናት እና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
ግልፅ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ ጨረታ መለያ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 የቀስተ ደመና አፀደ ህፃናት እና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት.1 አላቂ የቢሮ እቃዎች አላቂ የትምህርት እቃዎች ሲፒኦ 20,000
- ሎት.2 የጽዳት እቃዎች ሲፒኦ 25,000
- ሎት.3 የደንብ ልብስና የደንብ ልብስ ስፌት ሲፒኦ 25,000
- ሎት 4 ለተለያዩ ጥገና የሚውሉ አላቂ እቃዎች ሲፒኦ 5,000
- ሎት.5 ቋሚ መገልገያ እቃዎችና መሳሪያዎች ሲፒኦ 20,000
- ሎት 6 የኮምፒውተር ፎቶ ኮፒ ማባዣ ጥገናና ሌሎች ስራዎች ሲፒኦ 2,000
- ሎት 7 ህትመት ሲፒኦ 5,000
በዚህ መሰረት ከላይ በተዘረዘሩት እቃዎች ላይ ጨረታ መሳተፍ የምትፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች በሙሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባችሁ።
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመከፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- በአቅራቢነት የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው
- ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር( TIN) ያላቸው
- አምራች ሆነው በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ ከአደራጃቸው አካል የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት ማለትም ከሎት 1 -7 የሚሰላ ብር 2% በባንክ በተመሰከረለት የክፍያ ትዕዛዝ( CPO) ማስያዝ አለባቸው።
- የጨረታው ሙሉ ሰነድ የማይመለስ ብር 300( ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በቀስተ ደመና የመ/ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 14( ሪዳት ፋይናንስ ቢሮ) በመምጣት ሰነዱን መውሰድ ይቻላል።
- ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት አስር( 10) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የት/ቤቱ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 15 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዋጋ የተሞላበት ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻ በማሸግ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የሚያበቃው በአስረኛው ቀን ከቀኑ 11:30 ይሆናል።
- ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው ቀን ጠዋት 3:30 ታሽጎ ወዲያውኑ በዕለቱ 4:00 ሰዓት ላይ በት/ቤቱ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 15 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልፅ ይከፈታል።
- የጨረታው አሸናፊ አካል የውል ማስከበሪያ ላቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል። የውል ማስከበሪያ ሳያስይዙ ውል መዋዋል አይቻልም።
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ ሶስት ቀን በፊት ሳምፕል( ናሙና) ማቅረብ አለባቸው። ሳምፕል ያላቀረበ ተጫራች ለውድድር አይቀርብም።
- የጨረታው ሙሉ ሰነድ ሳይገነጠል መመለስ አለበት። ሙሉ ሰነድ ያላስገባ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይደረጋል።
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ያሸነፉትን ዕቃ በራሳቸው ትራንስፖርት ተቋሙ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ:- መሳለሚያ ወረዳ9 ከሞቢል ከፍ ብሎ እንገኛለን።
ለበለጠ መረጃ:- 011 2 13 50 68
ቀስተደመና ቅድመ አንደኛ፤ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
✨ messages.ai_summary
Keste Demena Kindergarten and Primary School (Addis Ketema Sub-city, Woreda 09) seeks suppliers in 7 lots: office and school consumables, cleaning items, uniforms and tailoring, maintenance items, fixed equipment, computer/copier repair and printing. Licensed VAT-registered suppliers. Open bid.
