ኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተተዉና የተወረሱ የተለያዩ ዕቃዎችን (አልባሳት፣ ጨርቃጨርቅ፣ ጫማዎች፣ ሽቶዎች፣ ኤሌክትሮኒክስና ሌሎች ዕቃዎች) በጨረታ ለመሸጥ ያወጣው ማስታወቂያ።
Modjo Customs Branch Office (የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)
የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ግ12/2019 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስመጪዎች በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 1160/2011 መሰረት የተተው ወይም የተወረሱ ዕቃዎችን በዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 9 መሠረት የተተውና የተወረሱ ንብረቶችን ማለትም POLYSTER KNITTED FABRIC MATERIAL፣ POWDER JACOBI ION EXCHANGE,LADY SKIRT,MEN T- SHIRT, LADY TIGHT AND OTHER PASSENGER LIFT,CASTROL OIL,HAIR STRAIGHTENER፣ የተለያዩ አልባሳት፣ ጫማዎች፣ ሽቶዎች፣ ፔርሙዝ፣ ቻርጀር እና ሌሎች እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: በዚህም መሠረት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን::
- ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት፣ ብዛት፣ የጨረታ ሠነድ እና መመሪያ ከአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በመግዛት ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ሲሆን አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል:: ተጫራቾች ከአክሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሰነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶችን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋት 2:00 እስከ ቀኑ 6:00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7:00 እስከ ቀኑ 10:30 እና ዓርብ ከጠዋት 2:00 እስከ ቀኑ 5:00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7:30 እስከ ቀኑ 10:30 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋት 2:00 እስከ ቀኑ 5:30 መመልከት ይችላሉ::
- የጨረታ ሰነዱን ከአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም /ድረገፅ/ አንላይን ላይ ብቻ መግዛት እና መጫረት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን ::
- ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ በአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ማያያዝ አለባቸው:: ሆኖም ግምታዊ ዋጋቸው ከብር 500,000.00 በታች የሆኑ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ::
- ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በ ETHIOPIAN CUSTOMS COMMISSION MODJO BRANCH OFFICE በሚል ሥም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአዲስ አበባ፤ አዳማ እና ሞጆ ቅርንጫፎች ብቻ አሠርተው አክሽን ኢትዮጵያ ሂደው በማስያዝ ወይም በአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ባለው የሲፒኦ አማራጮች አንላይን ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በመግዛት የሚወዳደሩበትን ዕቃ አስቀድሞ ለሚሞሉት ዋጋ ቅ/ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም:: በጨረታ ተሸጦ ለእቃውም የተከፈለ ገንዘብ አይመለስም::
- ተጫራቾች የአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር /AUCTION ETHIOPIA/ ብለው በማውረድ ወይም (AUCTION.ET/ ላይ መመዝገብ እና መጫረት ይችላሉ::
- የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 8ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 5:00 ሰዓት ድረስ በአክሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን ፕላትፎርም መወዳደሪያ ዋጋ ማስገባት ይችላሉ:: ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታውን ሂደትና ውጤት ኦንላይን መከታተል ይችላሉ::
- ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ 15% ቫትን ያካተተ መሆን አለበት::
- ማንኛውም በግልጽ ጨረታ የሚሳተፍ ተጫራች ጨረታው ከተጀመረ በኋላ ዋጋ መቀየር ወይንም የሌላ ተጫራቾችን ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ አሻሽሎ ማቅረብ አይችልም፤ በጨረታ ሽያጭ ውድድር ላይ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፤ ጨረታው ተጀምሮ ዋጋ ከሰጡ በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይቻልም እና የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል::
- የግልጽ ጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለበት:: በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ገንዘቡ ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ያስያዙት ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይደረጋል::
- በተራ ቁጥር 10 በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ ዕቃውን ያላነሳ/ያልተረከበ እንደሆነ ለሚቆይበት ለተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል:: ሆኖም ዕቃው በ2 (ሁለት) ወራት ውስጥ ካልወጣ እንደተተወ ተቆጥሮ በጨረታ ሽያጭ ይወገዳል::
- አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎችን ለመረከብና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይሸፍናል::
- ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጨረታ የአቀረበውን ዕቃ ብዛት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ሙሉ መብት አለው:: በጨረታ ተሸጦ በጨረታ አሸናፊው የተወሰደ ዕቃ አይመለስም::
- የአክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በአጭር ስልክ ቁጥር መስመር 9164 ወይም 09-05-11-55-11/011-666-8828 በመደወል ማግኘት ይቻላል::
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በሥልክ ቁጥር 022-236-90-94 /022-236-01-90 ላይ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::
በጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Ethiopian Customs Commission Modjo Branch sells abandoned and confiscated goods online via Auction Ethiopia, as is: polyester fabric, ion exchange powder, clothing, shoes, perfume, thermoses, chargers, Castrol oil, hair straighteners. Bidders need a sector trade licence, TIN, VAT and tax clearance.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
