Tender Detail

Tender Details

  • Company Bank of Abyssinia S.C. (አቢሲንያ ባንክ አ.ማ)
  • Address HQ Building, The Gambia st, Legehar, Addis Ababa, Ethiopia, Phone: 0115 15 07 11
  • Websitehttps://www.bankofabyssinia.com/
  • Deadline03 Dec 2026, 10:30 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት
  • opening dateህዳር 24 ቀን 2019 ዓ.ም የጨረታ ሰዓት 5:30-6:00
  • Categories Land , House, Building And Warehouse , Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale

አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውን እና በሠንጠረዥ ውስጥ የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) ለባንኮች በተሰጠው ስልጣን መሠረት ንብረት ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

Bank of Abyssinia S.C. (አቢሲንያ ባንክ አ.ማ)


በድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውን እና በሠንጠረዥ ውስጥ የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) ለባንኮች በተሰጠው ስልጣን መሠረት ንብረት ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

  • ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
  • የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።
  • ተበዳሪው /መያዣ ሰጪው/ በሐራጁ ቀን እና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ። ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
  • የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል። ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ለቀሪው የሊዝ ክፍያ ገዢው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል።
  • ንብረቱን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ወይም ማየት ይቻላል።
  • በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ /አሸናፊ/ ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል።
  • የጨረታ ቦታ አዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 7፣ ለገሀር በሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የፎርክሎዠር እና ዴት ሊቲጌሽን ዲቪዥን የጨረታ ክፍል ውስጥ ነው።
  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115 15 11 53 እና 0115 15 07 11 አ.አ በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
  • ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተ.ቁየተበዳሪው ስምየመያዣ ሰጪው ስምየንብረቱ አይነት እና አገልግሎትየቦታው ስፋት በካ.ሜየይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥርንብረቱ የሚገኝበት አድራሻየጨረታው መነሻ ዋጋ በብርጨረታው የሚካሄድበት ቀንየምዝገባ ሰዓትየጨረታ ሰዓት
1አቶ አበበ ምሲሳ ባይሳአቶ አበራ ደፋር ከተማለኢንዱስትሪ አገልግሎት የሚዉል ህንፃ/መጋዘን/፣G+2 ቢሮ እና G+1 የጥበቃ ቤት ያለዉ10,094.13OR003095212003ኦሮሚያ ክልል፣ ቢሾፍቱ ከተማ፣170,970,819.78ህዳር 24 ቀን 2019 ዓ.ም4:30-5:305:30-6:00
2አቶ አበበ ምሲሳ ባይሳኤጂኤም/AGM/ ኢንዱስትሪስ ኃ/የተ/የግ/ማህበርለኢንዱስትሪ አገልግሎት የሚዉል ህንፃ/መጋዘን/፣ G+1 ቢሮ እና G+1 ሁለት የጥበቃ ቤት ያለዉ10,222.12OR00011323028008ኦሮሚያ ክልል፣ሸገር ከተማ፣መልካ ኖና ክ/ከተማ /ታጠቅ አበባ/201,704,931.59ህዳር 24 ቀን 2019 ዓ.ም8:30-9:309:00 10:00
✨ messages.ai_summary
Bank of Abyssinia re-advertises the as-is auction of two foreclosed industrial properties in Oromia: a warehouse with G+2 office and G+1 guard house on 10,094.13 sq m in Bishoftu, and a warehouse with G+1 office and two G+1 guard houses on 10,222.12 sq m in Sheger city.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender