Tender Detail

Tender Details


የኩታበር ወረዳ ፍ/ቤት የጽሕፈት መሳሪያ፣ ቋሚ እቃ፣ የቢሮ ማሽነሪ፣ ህትመት፣ ደንብ ልብስ እና የፅዳት እቃዎች ግዥ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኩታበር ወረዳ ፍ/ቤት


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኩታበር ወረዳ ፍ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በጋዜጣ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን ሎት 1 አላቂ የጽሕፈት መሳሪያዎች ሎት 2 ቋሚ እቃ ሎት 3 የቢሮ ማሽነሪ፣ ሎት 4 ህትመት፣ ሎት 5 የደንብ ልብስ፣ ሎት 6 አላቂ የፅዳት እቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው።
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ/ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  6. የሚገዙ እቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (specification) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በኩታበር ወረዳ ፍ/ቤት ግዥ/ን/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 10 ከ27/2/2019 ዓ.ም ጀምሮ መግዛት ይችላሉ።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲ.ፒ.ኦ. ለሚወዳደሩበት ብር ወይም ለሚሰራው ስራ ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም ከታመነበት በባንክ በቼክ ማስያዝ አለባቸው።
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡንም ኦርጂናልና ኮፒ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በኩታበር ወረዳ ፍ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 10 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ቀን ከ27/2/2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 18/3/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ።
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 10 በቀን 18/3/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል። ተጫራቾች ለእቃው ዓይነትም ሆነ መጠን በጨረታው በሙሉ ወይም በከፊል መሳተፍ ይችላሉ። ሆኖም አንድ ተጫራች በአንድ ሎት ውስጥ ከተዘረዘሩት የእቃ ዓይነቶች መካከል ከፋፍሎ መጫረት አይችልም።
  11. መ/ቤቱ ጨረታውን በድምር ወይም በነጠላ ዋጋ የማወዳደር መብቱ የተጠበቀ ነው። መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ጨረታው በመሰረዙ ምክንያት ተጫራቾች ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ሃላፊነት አይወስድም።
  12. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0914068901 ወይም 0920794336 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኩታበር ወረዳ ፍ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Kutaber Woreda Court (Amhara) seeks suppliers in six lots: consumable stationery, fixed items, office machinery, printing, uniforms and cleaning supplies. Bidders may bid per lot but not split items within a lot. Open to licensed, VAT-registered suppliers with TIN.
Save Tender