አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውን በሠንጠረዥ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
Bank of Abyssinia S.C. (አቢሲንያ ባንክ አ.ማ)
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውን በሠንጠረዥ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ የቀረበዉን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታዉ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ወዲያዉ ይመለስላቸዋል፡፡
- ተበዳሪው /መያዣ ሰጪው/ በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል፡፡ ዉዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ለቀሪው የሊዝ ክፍያ ገዢው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል፡፡
- ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ወይም ማየት ይቻላል፡፡
- በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው አሸናፊ የጨረታ ከፍተኛ ዋጋ አቀራቢ /አሸናፊ/ ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል፡፡
- የጨረታው ቦታ ሐዋሳ ከተማ ባህል አደባባይ ክ/ከተማ አዳሬ ቀበሌ ዉስጥ በሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ ሐዋሳ ዲስትሪክት ሕንፃ 4ኛ ፎቅ ላይ ባለዉ የሕግ ክፍል ዉስጥ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115 15 11 53 እና 0115 15 07 11 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
| ተ.ቁ | የተበዳሪው ስም | የመያዣ ሰጪው ስም | የንብረቱ አይነት እና አገልግሎት | የቦታው ስፋት በካ.ሜ | የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር | ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ | የጨረታው መነሻ ዋጋ በብር | ጨረታው የሚካሄድበት ቀን | የምዝገባ ሰዓት | የጨረታ ሰዓት | ጨረታው የወጣዉ |
| 1 | አቶ አለሙ አመኑ | ተበዳሪዉ | የመኖሪያ ቤት | 463.75 | 2081 | አለታ ወንዶ ከተማ | 1,117,169.13 | ሕዳር 22 ቀን 2019 ዓ.ም | 4:30-5:30 | 5:30-6:00 | ድጋሚ |
| 2 | አቶ አለሙ አመኑ | አቶ አለማየሁ አለሙ | የንግድ ቤት | 265 | 2082 | አለታ ወንዶ ከተማ | 2,557,684.39 | ሕዳር 22 ቀን 2019 ዓ.ም | 8:30-9:30 | 9:30-10:00 | ድጋሚ |
| 3 | አቶ አለሙ አመኑ | ተበዳሪዉ | የመኖሪያ ቤት | 512.55 | 2283 | አለታ ወንዶ ከተማ | 1,040,408.24 | ሕዳር 23 ቀን 2019 ዓ.ም | 4:30-5:30 | 5:30-6:00 | ድጋሚ |
| 4 | አቶ አለሙ አመኑ | አቶ አለማየሁ አለሙ | የመኖሪያ ቤት | 645.09 | 2060 | አለታ ወንዶ ከተማ | 2,850,326.87 | ሕዳር 23 ቀን 2019 ዓ.ም | 8:30-9:30 | 9:30-10:00 | ድጋሚ |
| 5 | አቶ አለሙ አመኑ | ተበዳሪዉ | የንግድ ቤት | 799.18 | የይዞታ ልዩ መለያ ቁጥር SD001080402006 | ሐዋሳ ከተማ | 13,530,735.32 | ሕዳር 24 ቀን 2019 ዓ.ም | 4:30-5:30 | 5:30-6:00 | ድጋሚ |
| 6 | አቶ አለሙ አመኑ | ተበዳሪዉ | በካርታው ለመኖሪያ ቤት የተፈቀደ እና በግንባታ ላይ የሚገኝ | 1277.92 | የይዞታ ልዩ መለያ ቁጥር SD001080402002 | ሐዋሳ ከተማ | 44,549,306.66 | ሕዳር 24 ቀን 2019 ዓ.ም | 8:30-9:30 | 9:30-10:00 | ድጋሚ |
| 7 | አቶ አለሙ አመኑ | ተበዳሪዉ | የንግድ ቤት | 700 | የቦታ ልዩ መለያ ቁጥር HUB114/98CB-5 | ሐዋሳ ከተማ | 16,569,858.94 | ሕዳር 25 ቀን 2019 ዓ.ም | 4:30-5:30 | 5:30-6:00 | ድጋሚ |
✨ messages.ai_summary
Bank of Abyssinia auctions seven foreclosed properties of one borrower: residential and commercial houses in Aleta Wondo town, and commercial houses plus a residential building under construction in Hawassa town.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
