Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮ ጥሪት የበጎ አድራጎት ድርጅት
  • Address , Phone: 0999087535
  • Website
  • Deadline09 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 300.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityብር 10,000 (CPO ወይም የባንክ ዋስትና)
  • opening dateበ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት
  • Categories Accounting & Auditing , Audit Service

ኢትዮ ጥሪት ቻሪቲ ኦርጋናይዜሽን የ2018 በጀት ዓመት የሂሳብ አፈጻጸም ሪፖርትን እና የሂሳብ ሰነዶችን ኦዲት ለማስደረግ ብቃትና ሕጋዊ ፈቃድ ካላቸው የኦዲት አገልግሎት ሰጪዎች በግልጽ ጨረታ የዋጋና የቴክኒክ ብቃት ውድድር አድርጎ ማሰራት ይፈልጋል።

በኢትዮ ጥሪት የበጎ አድራጎት ድርጅት


የጨረታ ማስታወቂያ

ኢትዮ ጥሪት ቻሪቲ ኦርጋናይዜሽን የ2018 በጀት ዓመት የሂሳብ አፈጻጸም ሪፖርትን እና የሂሳብ ሰነዶችን ኦዲት ለማስደረግ ብቃትና ሕጋዊ ፈቃድ ካላቸው የኦዲት አገልግሎት ሰጪዎች በግልጽ ጨረታ የዋጋና የቴክኒክ ብቃት ውድድር አድርጎ ማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆነም በዘርፉ ተገቢው ሕጋዊ ፈቃድ፣ ሙያዊ ብቃትና ልምድ ያላቸው የኦዲት አገልግሎት ሰጪዎች የጨረታ ሰነዳቸውን በማቅረብ እንዲወዳደሩ ጥሪ ያቀርባል።

ተ.ቁ የግዥው ዓይነት የጨረታ መለያ ቁጥር ምድብ/ሎት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር መጠን ጨረታው የሚዘጋበት ቀንና ሰዓት ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት
1 የግዥው ዓይነት፣ የኦዲት አገልግሎት ግዥ (የ2018 በጀት ዓመት የሂሳብ አፈጻጸም ሪፖርትና የሂሳብ ሰነዶች ኦዲት) በግልጽ ጨረታ የቴክኒክ ብቃትና የዋጋ ውድድር። ETCO/01/2019 01/2019 10000 ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ በተከታታይ የሚቆጠር ቀን ሆኖ በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ በተከታታይ የሚቆጠር ቀን ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት

በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፣

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ጠናቀው ስለመከፈላቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው፡፡
  2. በጨረታ ለመሳተፍ የሚችሉ መሆኑን ከኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የድጋፍ ደብዳቤ የሚያቀርቡ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ(TIN)ያላቸው፣
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በኢትዮ ጥሪት ቻሪቲ ኦርጋናይዜሽን ስም CPO ወይም በባንክ ዋስትና የተረጋገጠ ተዘጋጅቶ መቅረብ አለበት፡፡
  6. ከላይ የተገለጸውን መስፈርት አሟልተው በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከላይ በሰንጠረዥ ከተጠቀሰው የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት በስራ ሰዓት ከድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 01 ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1 እስከ 10 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ከቴክኒክ መወዳደሪያ ሰነድ ጋር አያይዘው በቴክኒክ ኢንቨሎፖች ውስጥ ማቅረብ አለባቸው፡
  8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ቴክኒካል ዋናና ኮፒ እና የፋይናንሻል ማስረጃዎችን ዋናና ኮፒ በመለየት ዋና እና ኮፒ በአንድ ፖስታ ካኪ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ከላይ በሰንጠረዥ ከተጠቀሰው የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት በቢሮ ቁጥር 01 ለዚሁ ለተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ተጫራቾች በጨረታ ሰነዳቸው ላይ እና በፖስታው ላይ የድርጅቱን ማህተም ፊርማ ማድረግ አለባቸው፡
  9. ዘግይተው የደረሱ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፤ መ/ቤቱ የተሻለ ምንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፣ ገላን ኮንደሚኒየም፣ ሴንትራል ሕንፃ ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁ 0999087535 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ ።

በኢትዮ ጥሪት የበጎ አድራጎት ድርጅት

✨ messages.ai_summary
Ethio Tirit Charity Organization seeks legally licensed, qualified audit service providers to audit its 2018 budget year financial performance report and accounting documents via open bid with technical and price competition. Bidders need a renewed trade license, tax clearance, TIN, VAT registration, and a support letter from the Ethiopian Revenues and Customs Authority.
Save Tender