Tender Detail

Tender Details

  • Company የአብክመ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልድያ ቅርንጫፍ
  • Address , Phone: 0334319805
  • Website
  • Deadline02 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 500.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityሎት 1-7 ከብር 3,000 እስከ ብር 15,000፤ ሎት 8 ብር 480,000 (CPO፣ የባንክ ዋስትና ወይም LC)
  • opening dateበዚሁ ቀን 4:30
  • Categories Building Construction , Ict Equipment'S And Its Accessories , Office And Home Furniture

ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ የጽዳትና ጽህፈት እቃዎች፣ ደንብ ልብስ፣ የመኪና እቃ፣ ዘይት እና የህንፃ እድሳትና ግንባታ ግዥ (8 ሎት) - የአብክመ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልድያ ቅርንጫፍ

የአብክመ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልድያ ቅርንጫፍ


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የአብክመ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልድያ ቅርንጫፍ የተለያዩ ሎት1. ኤሌክትሮኒክስ ሎት2. ፈርኒቸር ሎት3. የጽዳት እቃ ሎት4. የጽህፈት መሳሪያ ሎት5. የደንብ ልብስ ሎት6. የመኪና እቃ ሎት7. ዘይትና ቅባት መግዛትና ሎት8. የህንፃ እድሳት፣ የሳይት ወርክ እና የበግ ማቆያ የሀንፃ የግንባታ ስራዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች ለመሳተፍ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. የታደሰ ንግድ ፈቃድ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. የግብር መከፈያ ቁጥር /ቲን ነበር/ ያላቸው ፤
  3. ግዥው ከ500,000/ከአምስት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆነና ማቅረብ የሚችል
  4. ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት ግብር የከፈሉበትን ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል
  5. ተጫራቾች ከሚያቀርቧቸው ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማህተም፣ ፊርማና ስም በሚነበብ መልኩ መጻፍና በየገጹ ማህተም ማድረግና መፈረም ይጠበቅባቸዋል
  6. ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ማንኛውንም የመንግስት ግብር እና ታክስን ያካተተ ዋጋ መሆን አለበት።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒ በማድረግ በፖስታ አሽገው ማቅረብ እና በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  8. ውድድሩ በጠቅላላ ዋጋ ወይም በሎት መሆኑ ታውቆ ሁሉንም መሙላት አለባቸው።
  9. ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸላቸው ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት መጥተው ውል መውሰድ እና በውሉ ላይ በተቀመጠው ቀነ ገደብ በውሉ መሰረት መፈጸም አለበት ።
  10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ከሎት 1 እስከ ሎት 7 ላሉት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት በ10 ተከታታይ ቀናት እና ሎት 8 ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በአብክመ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልድያ ቅርንጫፍ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ድረስ በመምጣት የማይመለስ ብር 500.00/አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ገዝተው መውሰድ ይችላሉ ።
  11. የጨረታ ሳጥኑ ከሎት 1 እስከ ሎት 7 ያለው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን እና ሎት 8 ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በወጣ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4:30 ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ።
  12. በጨረታው ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታው በሌሉበት የሚከፈት ሆኖ በግዥ መመሪያ ቁጥር 144 /2018 መሰረት ተግዥ ይሆናል።
  13. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የማብራሪያ ጥያቄ ካላቸው ከጨረታ መክፈቻ ጊዜው ከ5 ቀን በፊት ለኢንስቲትዩቱ ቅርንጫፍ ማሳወቅ አለበት።
  14. የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ሎት1. 11,500.00 ብር ሎት2. 15,000.00 ብር ሎት3. 11,500.00 ብር ሎት4. 11,500 00. ብር ሎት5. 3,000.00 ብር ሎት6. 12,000.00 ብር ሎት7. 13,000.00 ብር ሎት8. 480,000 .00 ብር በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በሲ.ፒ.ኦ ፣ ከባንክ በሚገኝ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት እና የጨረታ ማስከበሪያ ሰነዶች ጋራንቲታቸው ከ3/ሶስት/ ወር ወይም ከ90 ቀን ማነስ የለበትም።
  15. የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ ማስረጃና የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም
  16. በነጠላም ሆነ በጠቅላላ ዋጋ የተሳሳተ/ስርዝ ድልዝ/ የጨረታ ሰነድ ማቅረብ ከጨረታ ውጪ ያደርጋል
  17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  18. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በካላንደር ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት 4:30 የሚከፈት ይሆናል።
  19. የግንባታ ስራ ግዥ ደረጃ 5 GC እና በላይ ተቋራጮች መሆን አለባቸው።

ማሳሰቢያ
ተጫራቾች ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0334319805 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ።

የአብክመ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልድያ ቅርንጫፍ

✨ messages.ai_summary
The institute seeks suppliers for 8 lots: electronics, furniture, cleaning supplies, office supplies, uniforms, vehicle supplies, oil and lubricants, and building renovation/site work including a sheep shed. Bidders need a renewed trade license, TIN, VAT registration if above 500,000 birr, and tax clearance. Construction requires Grade 5 GC or higher.
Save Tender