Tender Detail

Tender Details

  • Company Kombolcha Customs Branch (የኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)
  • Address Ethiopia Kombolcha City, Kembolcha, Ethiopia, Phone: 0116730520
  • Website
  • Deadline28 Oct 2026, 9:50 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 100 (የማይመለስ)
  • Bid Securityግልፅ ጨረታ የዋጋው 5%፤ ሐራጅ ብር 200,000 (ከ2 ሚሊዮን በላይ) / ብር 100,000 (ከ2 ሚሊዮን በታች) (CPO)
  • opening dateበ6ኛው ቀን 4:00 (ግልፅ) / 4:30 (ሐራጅ)
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale

በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተለያየ ጊዜ ውርስ የተደረጉ WHEEL LOODER፣ BAJAJ፣ ተሽከርካሪ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ጫማ፣ አልባሳት፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የቧንቧ ብረት እና ምግብ ነክ በግልፅ እንዲሁም አንበር የገና አባት ልብስ /santasuit/ እና ኮስሞቲክስ በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል።

Kombolcha Customs Branch (የኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)


ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር -11/2019 ዓ.ም

በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተለያየ ጊዜ ውርስ የተደረጉ WHEEL LOODER፣ BAJAJ፣ ተሽከርካሪ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ጫማ፣ አልባሳት፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የቧንቧ ብረት እና ምግብ ነክ በግልፅ እንዲሁም አንበር የገና አባት ልብስ /santasuit/ እና ኮስሞቲክስ በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ ሲሆን መስፈርቶቹም:-

  1. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የፀና የንግድ ፈቃድ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር መ/ቤት የሚሰጥ የምስክር ወረቀት (ክሊራንስ) እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል ሲሆን ተሽከርካሪ መጫረት ለምትፈልጉ ንግድ ፈቃድ የማይጠይቅ በመሆኑ ማንኛውም ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ግለሰብ መጫረት ይችላል።
  2. የዚህ አንቀፅ ተራ ቁጥር (1) ድንጋጌ ቢኖርም ግምታዊ ዋጋው ከብር 2 ሚሊዮን በታች የሆነ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት (ሰርተፍኬት) ማቅረብ አያስፈልገውም።
  3. በጨረታ የሚሸጠው ዕቃ በኮሚሽኑ ቁጥጥር ስር ከመግባቱ በፊት ባለቤት የነበረ ወይም የባለቤቱ ወኪል ወይም ቤተሰብ የሆነ ሰው በማንኛውም መልክ በጨረታው መሳተፍ አይችልም።
  4. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ አይነትና ብዛት የጨረታ ሰነድና መመሪያ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) እየከፈሉ ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው (6) ቀን 3:00 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታው የዕቃዎችን ዝርዝር በያዘው ሰነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ሥር የሚገዙበትን ዋጋ በአሀዝና በፊደል ገልፀው እና በተራ ቁጥር 1 ላይ የተገለፁትን በኤንቬሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን 3:50 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው።
  6. የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ስድስተኛው ቀን በጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚካሄድ ሲሆን ግልፅ ጨረታው 3:50 ሰዓት ተዘግቶ 4:00 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ሀራጅ ጨረታው 4:30 ሰዓት የሚጀምር ይሆናል።
  7. ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ05 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በመክፈል ንብረቶቹን ማንሳት ይኖርባቸዋል። በተሰጠው የጊዜ ገደብ ክፍያው የማይወስዱ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው እንደገና ለጨረታ ይቀርባል።
  8. ተጫራቾች ለዕቃዎች በሚያቀርቡት የመጫረቻ ዋጋ አሸናፊ ከሆኑ ተጨማሪ እሴት ታክስ 15% (VAT) የሚጨመርበት ይሆናል።
  9. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን ድረስ ለሽያጭ የተዘጋጁ ዕቃዎቻችን በኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ8:00 ሰዓት እስከ 10:00 ሰዓት ድረስ እና ስድስተኛው ቀን ጠዋት 3:00 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ።
  10. ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታ ዕቃዎች የሰጡትን የመግዣ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) እና ለሀራጅ ጨረታ የዕቃው መነሻ ዋጋ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ለሆነ ዕቃ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ ብር እንዲሁም የዕቃው መነሻ ዋጋ ከ2 ሚሊዮን ብር በታች ለሆነ ዕቃ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 100,000 /መቶ ሺህ/ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
  11. መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 033 551 06 93 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
The Kombolcha Customs Branch is selling assorted seized goods—wheel loaders, Bajaj vehicles, electronics, footwear, clothing, vehicle spare parts, steel pipes, food items, Santa suits, and cosmetics—via open and auction bids. Bidders need a relevant trade license, VAT registration, tax clearance, and TIN; vehicle bidders need only ID (18+).
Save Tender