በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 ሰሚት ጤና ጣቢያ ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን አቅራቢዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 ሰሚት ጤና ጣቢያ
የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 01/2019
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 ሰሚት ጤና ጣቢያ ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን አቅራቢዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ሰዓት ለ10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት በጤና ጣቢያው ፋይናንስ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡
ከተለያዩ ሕጋዊ አቅራቢዎች አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባችሁ፡-
- የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው
- የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት
- የዘመኑን ግብር ስለመክፈሉ የሚያረጋግጥ ማስረጃ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ያለው
የጨረታ ማስከበሪያ በተጫራቹ ዘርፍ የሞሉትን በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡
የተጫራቾች መመሪያ
- ሎት1.ደንብ ልብስ፡….10000 ( አስር ሺ ብር)
- ሎት 2.የጽሕፈት መሣሪያና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች--10000 (አስር ሺ)
- ሎት3. ሕትመት ….10000 ( አስር ሺ ብር)
- ሎት 4. መድኃኒትና የላብራቶሪ ሪኤጀንቶች--10000 (አስር ሺ)
- ሎት 5. ኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ….30000 (ሰላሳ ሺ ብር)
- ሎት6. የፅዳት ዕቃዎች—--10000( አስር ሺ ብር)
- ሎት7.የእንጨትና የብረት ውጤቶች….. 10000 ( አስር ሺ)
- ሎት8.የግንባታ ሥራዎች---20000 ( ሃያ ሺ)
የጨረታ ዋጋ የሚሞላው ከጤና ጣቢያው በዝገት ሰነድ ላይ ሲሆን የሚወዳደሩበትን ዘርፍ ዋጋ በመሙላት ማህተምና ፊርማ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ሰነዱን ሲሞሉ ፊደል ስርዝ ድልዝ ማድረግ የለባቸውም፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የአቅርቦት ዘርፍ ነጠላ ና ጠቅላላ ዋጋ ማሳየት አለባቸው፡፡ የሚሞላት የነጠላና ጠቅላላ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን /ቫትን/ ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች ያቀረቡት ቋሚ ዕቃ ከሆነ ለሚሰጠው አገልግሎት ቢያንስ የአንድ ዓመት ዋስትና ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ቴክኒካል ዶክመንት ኦሪጅናሉ እና ሲፒኦ በአንድ ፖስታ በማሸግ፣ ፋይናንሻል ኦሪጅናል ሰነድ በአንድ ፖስታ፣ በማሸግ እነዚህን ኦሪጅናል የሚል ጽሑፍ መጻፍ፤ ቴክኒካል ዶክመንት ኮፒ እና ፋይናንሻል ሰነድ ኮፒ በአንድ ፖስታ በማሸግ እነዚህን ኮፒ ጽሑፍ መጻፍ
- ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋ በሞሉበት የጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ ገጽ ላይ እና በየፖስታዎቹ በታሸጉት ፖስታዎች ላይ የድርጅቱን የሰሌ ጋሀኔ ፊርማና ስም እንዲሁም ሕጋዊ ክብ ማህተም ማሳረፍ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1- 4 በተዘረዘረ መሰረት የሞሉትንና ያዘጋጁትን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10(አስር) የሥራ ቀናት በመንግሥት የሥራ ሰዓት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው 5 በጤና ጣቢያው የግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 414 በተቀመጠው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ የጨረታ ሣጥኑ በ11ኛ (አስራ አንደኛው) የሥራ ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ የሚዘጋ ሲሆን የተጠቀሰው ጊዜ ካለፈ በኋላ የሚቀርቡ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
ጨረታው በጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ በጤና ጣቢያው አዳራሽ ይከፈታል፡፡ - በተጫራቾች የተሞላው የጨረታ ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60/ስልሳ/ ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ይሆናል ፡፡
(የተቀሩት ቁጥር 7-19 ዝርዝር መመሪያዎች፣ የጥቃቅንና አነስተኛ ድጋፍ ደብዳቤ እና ጥብቅ ማሳሰቢያዎች በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ይገኛሉ። የመድኃኒትና የላብራቶሪ ሪኤጀንት አቅራቢዎች የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPO (ሲፒኦ) ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡)
ተጫራቾች ስለ ጨረታው ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09-43-58-44-44 ቁጥር 407 በግንባር በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የለሚኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 ሰሚት ጤና ጣቢያ
