ግራንድ ማይክሮ ፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አ.ማ የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ቀልጣፋ የብድርና የቁጠባ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ ተቋም ሲሆን፤ፍላጎት ያላቸውን የውጪ ኦዲት ድርጅቶች ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ ለ3 (ሶስት) ተከታታይ የበጀት አመት የአክሲዮን ማህበሩን ሂሳብ ኦዲት እንዲያደርጉ ተቋማትን ይጋብዛል::
Grand Microfinance Institiution S.C (ግራንድ ማይክሮፋይናንስ ተቋም አክስዮን ማህበር)
ግራንድ ማይክሮ ፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አ.ማ
የውጪ ኦዲተር ጨረታ
ግራንድ ማይክሮ ፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አ.ማ የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ቀልጣፋ የብድርና የቁጠባ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ ተቋም ሲሆን፤ፍላጎት ያላቸውን የውጪ ኦዲት ድርጅቶች ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ ለ3 (ሶስት) ተከታታይ የበጀት አመት የአክሲዮን ማህበሩን ሂሳብ ኦዲት እንዲያደርጉ ተቋማትን ይጋብዛል:: በመሆኑም በጨረታው ላይ የሚሳተፉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል::
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ ታክስ ክሊራንስ፤የቫት ምዝገባና የግብር ከፋይ መለያ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል፤
- በኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ የፋይናንስ ተቋማትን ኦዲት ለማድረግ ፈቃድ የተሰጠውና የታደሰ የምዝገባ ፈቃድ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል፤
- ፍላጎት ያላቸው ድርጅቶች በሂሳብ እና ኦዲት ቦርድ (AABE) መመሪያ ቁጥር 1096/2025 ላይ የተቀመጡትን የኦዲት መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን ይኖርባቸዋል፤
- በሥራው ማለትም በፋይናንስ ተቋማት በተለይም የአነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት ኦዲት በማድረግ በቂ ልምድ ያለው፤
- የብሔራዊ ባንክ መመሪያ /DIRECTIVE NO.MFI/37/2024/ መሰረት የሚያሟላ
- አለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት የተከተለ ሂሳብ ኦዲት ያደረገና ልምድ ማቅረብ የሚችል፤
- የሚቀርበው የጨረታ ዋጋ ከ2019-2021 ዓ.ም ደረስ ያለው የሶስቱንም አመት ያካተተ መሆን ይኖርበታል::
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥቅምት 20/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ይከፈታል::
- ግራንድ ማይክሮፋይናንስ አ.ማ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ስለሆነም ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በዋናው መስሪያ ቤታችን ደብረዘይት በሚወስደው መንገድ በቅሎ ቤት ናክ ማደያ አጠገብ በሚገኘው ጋራድ ሞል 7ኛ ፎቅ ላይ በስራ ሰዓት በአካል በመቅረብ የሚሰራበትን ዝርዝር ማብራሪያውንና ዋጋ (Technical and Financial Proposal) ከአስፈላጊ ሰነዶች ጋር በማያያዝ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን TOR በተጠቀሱ ቀናት ዋናው ቢሮ በመቅረብ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን::
ግራንድ ማይክሮፋይናንስ ተቋም አክስዮን ማህበር
ስልክ ቁጥር 251-11-470-51-02
✨ messages.ai_summary
Grand Microfinance Institution S.C seeks external audit firms to audit its accounts for three consecutive fiscal years starting 2019 E.C. Bidders must have a renewed business license, tax clearance, VAT and TIN registration, AABE registration to audit financial institutions, relevant microfinance audit experience, and IFRS compliance per National Bank directive MFI/37/2024.
Not stated in the notice: bid security, bid document price. Check the original document or ask the issuer.
