በጉምሩክ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተያዙና የተወረሱ ተሽከርካሪዎችና ልዩ ልዩ ዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 15/2019
በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
የተያዙና የተወረሱ ተሽከርካሪዎችና ልዩ ልዩ ዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 15/2019
በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በሐራጅ ጨረታ እንዲሁም የተለያዩ ንብረቶችን (የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ ሞባይሎች፣ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውብት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን) በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በታች በቅፁ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ተሽከርካሪዎችን እና ንብረቶች ዝርዝር መረጃና መስፈርቶች ተዘጋጅቶ ከሀሙስ ጥቅምት 12/2019 ዓ.ም ጀምሮ ለተጫራቾች በአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ (አፕሊኬሽን) ወይም www.auction.et ላይ በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ላይ የሚታወቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ማሳሰቢያ፡ ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
በመሆኑም
- በዕቃ ግልፅ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀና የንግድ ፍቃድ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ፎቶ በማንሳት(ስካን በማድረግ) አንላይን የአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ ወይም www.auction.et ማያያዝ ይኖርበታል።
- በተሽከርካሪ ሐራጅ ጨረታ ለመሳተፍ ማንኛውም ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም (C.P.O) ሲ.ፒ.ኦ. በአካል ወደ አክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ወይም ቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን አክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡
- በጨረታው ላይ የዕቃው ወይም የተሽከርካሪው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሳተፍ አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች የዕቃዎቹን ጨረታ ሰነድ ከሀሙስ ጥቅምት 12/2019 ዓ.ም ጀምሮ በማንኛውም ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በአንላይን በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- በዕቃ ግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በቅ/ጽ/ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA KALITY CUSTOMS BRANCH OFFICE በባንክ አሰርተው ያሰሩትንም ሲ.ፒ.ኦ. በአካል ወደ አክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው ወይም ቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን አክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
- የተሽከርካሪ ሐራጅ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ለአያንዳንዱ ተሽከርካሪ ብር 200,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በተ.ቁ 5 በተገለጸው አድራሻ ተጫራቹ ማስያዝ አለበት፡፡ ያሰሩትንም ሲ.ፒ.ኦ. በአካል ወደ አክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው ወይም ቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን አክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት መጫረት ይችላሉ፡፡
| ተ.ቁ | የቅ/ጽ/ቤቱ ስም | የጨረታው አይነት | የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነድ ከወሰዱ ቀን ጀምሮ | የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት |
| 1 | አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት | የዕቃ ግልፅ | እስከ 17/02/2019 | 18/02/2019 3:45 ተዘግቶ በዚያው ቀን 4:00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ |
| 2 | የተሽከርካሪ ሐራጅ | እስከ 18/02/2019 | እስከ 19/02/2019 (ከ4:00 ሰዓት ጀምሮ አንላይን ላይ ለየምድቦቹ በተሰጠው ደቂቃ) መሠረት ይካሄዳል። |
8. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- ሙሉ በሙሉ የአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ ወይም www.auction.et (በኦንላይን) የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ የጨረታውን ሂደት በኦንላይን መከታተል ይችላሉ፡፡
9. ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
10. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡
11. ከላይ በተ/ቁ 10 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበ ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
12. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ መረጃ ለማግኘት፡- በስልክ ቁጥር 09-05-11-55-11
አድራሻ፡- ቦሌ አትላስ አውሮፓ ህብረት ዝቅ ብሎ ከለላ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 301 (ኦክሽን ኢትዮጵያ)
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ፡- 011-470-85-03
አድራሻ፡- ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው ወደ ኮዬ ፈጬ መንገድ መንገጠያ ፊት ለፊት ያለው ህንጻ
