የውጪ ኦዲት አገልግሎት (IFRS, 2019 ዓ.ም ጀምሮ ለ3 አመታት) - የአራዳ አትክልት ተራ የገበያ ማዕከል አ.ማ
Arada Atkilt Tera Market Center
የኦዲት ሥራ ጨረታ ማስታወቂያ
የአራዳ አትክልት ተራ የገበያ ማዕከል አ.ማ ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ በቀጣይ ሶስት አመታት የአክሲዮን ማህበሩን በ IFRS የተሰራ ሂሳብ በተፈቀደላቸው የውጪ ኦዲተሮች ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል፡፡
ተጫራቾች የሚከተሉት መስፈርቶች አሟልተው መወዳደር ይችላሉ፤
- የኢትዮጵያ የሂሳብ እና ኦዲት ቦርድ AABE 2018 ዓ.ም ኦዲት ፍቃድ ያለው፤
- ከIFRS ጋር የተጣጣሙ የሂሳብ መግለጫዎችን ኦዲት በማድረግ ልምድ ያለው በተለይ በተመሳሳይ ተቋማት ኦዲት ያደረገ፤
- በሞያው 10 አመትና ከዚያ በላይ የኦዲት ሥራ ልምድ ያለውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፤
- የ2018 ወይም 2019 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበ፤
- ተወዳዳሪዎች ለአገልግሎቱ በየበጀት አመቱ የሚያስከፍሉትን ዋጋ ንድፈ ሃሳብ/ፕሮፓዛል እና ሥራውን ሰርቶ የሚያጠናቅቅበትን ጊዜ እና የሂሳብ ምርመራውን አጠናቆ ሪፓርቱን የሚያስረክብበትን ጊዜ መግለጽ ይኖርበታል፡፡
ተወዳዳሪዎች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉ 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ መሰረት ሰነዶችን በታሸገ ኢንቨሎፕ እንዲያቀርቡ እንጋብዛለን፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ማክሰኞ ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ነው፡፡
አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0935 401595/96 ማግኘት ይቻላል
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከተማ ክ/ከተማ አራዳ ወረዳ 1 የቤ.ቁ አዲስ ፒያሳ አትክልት ተራ ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር ጂ4-024
አራዳ አትክልት ተራ የገበያ ማዕከል አ.ማህበር
✨ messages.ai_summary
Arada Atkilt Tera Market Center seeks licensed external auditors to audit its IFRS-compliant financial statements for three consecutive years starting from 2019 E.C. Bidders must hold a valid AABE audit license, have IFRS audit experience (especially for similar institutions), 10+ years of audit experience, renewed business license and registration, and VAT registration.
Not stated in the notice: bid security, bid document price. Check the original document or ask the issuer.
